ሁለት አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8C%8B%E1%8D%8B-%E1%88%99%E1%8B%9A%E1%89%80%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A8%E1%8B%9A%E1%88%85-%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%88%9E%E1%89%B5/

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010) ሁለት አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

አንጋፋዋ የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋች እና ክራር ደርዳሪ ጸሃይቱ ባራኪ በ 79 ዓመቷ ህይወቷ አልፏል።

የክቡር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል ባልደረባ፣የሙዚቃ አቀናባሪ እና ደራሲ ሻለቃ ግርማ ሃድጎም በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበራቸው ሁለቱ ኤርትራውያን ህይወታቸው ያለፈው በዚህ በያዝነው ሳምንት ነው።

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1931 ኤርትራ የተወለደችው ታዋቂዋ የትግርኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጸሃይቱ ባራኪ በ79 አመቷ በትውልድ ሃገሯ ኤርትራ ህይወቷ ማለፉ ታውቋል።

ጥቅምት 29/1921 የተወለዱት ሻለቃ ግርማ ሃድጉ በ90 ዓመታቸው በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ፊኒክስ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

The post ሁለት አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.