ህብረተሰቡ ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸዉ ጥያቄዎች ስራችንን እያስተጓጎለብን ነዉ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

Source: https://mereja.com/amharic/v2/190495

ከወሰን ማስከበር እና ካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች ችግር እየፈጠሩበት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የመንገድ ግንባታዎች ከወሰን ማስከበር እና ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ፣ህብረተሰቡ የሚያነሳዉ ጥያቄ ግንባታቸዉ እንዲጓተት እያደረገ ነዉ ብሏል፡፡
በባለስልጣኑ የአለም ገና መንገድ አዉታር እና ደህንነት ዳይሬከተር አቶ ኡመር ሁሴን፤በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከፊቼ እስከ ጉኃፅዮን ድረስ ያለዉን መንገድ የመጠገን ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዉ፤ ህብረተሰቡ ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸዉ ጥያቄዎች ስራችንን እያስተጓጎለብን ነዉ ብለዋል፡፡

በተለይም ገብረ ጉራቻ፣ ፍቼ እና ጓኃፅዮን እና በሌሎችም የዞኑ አካባቢዎች በካሳ ጥያቄ ምክንያት፣ግብአት ማምረቻ ለማግኘት መቸገሩንም ባለስልጣኑ አስታዉቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የወሰን ማስከበር እና የካሳ ክፍያ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለመፍታት፣ ከከተማ አስተዳደሮች ጋር እየመከረ እንደሚገኝም አቶ ኡመር ተናግረዋል፡፡
ችግሩ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚገኝ ያስታወቁት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡
ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ በፈጣን መንገዶች ግንባታ ላይም ተመሳሳይ ችግር እንደሚስተዋልም ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬከተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣በመገንባት ላይ ከሚገኙት የፈጣን መንገዶች መካከል ከዝዋይ -አርሲ ነጌሌ እና ከአርሲ ነጌሌ- ሃዋሳ ድረስ ያሉት መንገዶች፣ በግንባታዉ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ቤቶች እና ንብረቶች በተቀመጠላቸዉ የጊዜ ገደብ ባለመነሳታቸዉ ግንባታቸዉ እንደተስተጓጎለ ተናግረዋል፡፡
ችግርሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ዉይይት መደረጉን የተናገሩት አቶ ሳምሶን ህብረተሰቡም ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
Source

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.