ህብረተሰቡ የኢሬቻ በዓልን በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባ ገደዎች አሳሰቡ

ህብረተሰቡ የኢሬቻ በዓልን በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባ ገደዎች አሳሰቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሞ ወጣት የኢሬቻ በዓልን በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባገዳዎቹ አሳስበዋል፡፡

የኦሮሞ የአባገዳዎች ህብረት በሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል አከባበር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የወቅቱ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል በውስን ሰው እንዲከበር መወሰናቸውን አባገዳዎቹ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡም እራሱን እና ቤተሰቡን ከኮቪድ 19 በመጠበቅ በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ አሳስበዋል፡፡

እንዲሁም የኢሬቻ በዓል የሰላም ፣ የፍቅር እና የምስጋና በዓል ነው ያሉት አባ ገዳዎቹ መላው የኦሮሞ ወጣት በዓሉን ከፖለቲካ በጸዳ መንገድ እንዲያከብር ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ህብረተሰቡ የኢሬቻ በዓልን በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲያከብር አባ ገደዎች አሳሰቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply