ህወሃት ትግራይን ለመገኝጠል መንደር ለመንደር እየተሽለኮለ የትግራይን ህዝብ እያነጋገረ ነው።

Source: http://welkait.com/?p=10544
Print Friendly, PDF & Email

(የትግራይ ጉዳይ…) የኢትዮጵያ ህዝብ ነቅተህ ለሉኣላዊ ሀገርህና ለአንድነትህ ዘብ ቁም!!!!!!!!!

(ከአሰገደ ገብረ ሥላሴ)

በሰሜኑ ክፍለ ሀገራችን እየተናፈሱ ያሉ በጠባብነት መርዝ የተነከሩ ኣየሩን እየበከሉት ይገኛሉ። በኣሁኑ ጊዜ ቀደም ሲል ኢሳእያስ ኣፈወርቅ ካሁን በፊት ያልነበረው መለሳለስ በተለይ ከኣፍሪካ ቀንድ ካሉት ጎረቤት መንግስታት እና ሀገራት የነበረንን ሸካራ ግንኝነት በመሻሻል እንታረቅ ኣለን ብሎ ሲናገር ተደምጧል።

ኣሁን በቅርብ ደግሞ ከትግራይ ክልል የሚናፈሱ ያሉ ኣስደንጋጭ ወሬዎች ድሮውን ብዙ ሊሂቃን ዜጎች እንዲሁም ህወሃት ትግራይን ለመገኝጠል መንደር ለመንደር እየተሽለኮለ የትግራይን ህዝብ እያነጋገረ ነው!

የኣገር ኣንድነት ወዳድ ህዝቦች በስጋት ይመለከቱት የነበረ፣ ኣሁን ያ ተደብቆ የነበረ ኣገር በታኝ ጠባብነት ወደ በተግባር ለመፈጸም፣ በኣንድ ኣንድ ፍጡራን ተብዬዎች ኣንቀጽ 39 ህገመንግስት መብታችን፣ በመጠቀም ተገንጥለን ከኤርትራ ኣንድ በመሆን ጠንካራ የሰሜን ሃይል ለመሆን ኣይሻለንም ወይ በማለት መንደር ለመንደር እየተሽለኮለኩ መርዛቸውን እየረጩ ይገኛሉ ።

በሌላ በኩል ተጀምሮ ሳያልቅ ተቋጭቶ ተንሳፍፎ የሚገኜው የህውሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባም የኣንቀጽ 39 የመተግበር ጉዳይ ተነስቶ ኣጨቃጫቂ በመሆኑ በልዩነት እንደተበተኑ ከፕላኔት የተናፈሱ ምንጮች ይጠቁማሉ ።

ይህ ኣደገኛ የሃገር ለኣላውነታችን በመበታተን የባንዳዎች ተልእኮ ለመፈጸም የሚንቀሳቀሰው ያለው ቡዱን ኣመንጩ ማነው ለማለት ባይቻልም ፣ ሃቁ ግን ወላጆቻችን እንደዚህ ኣይነት ሲነገር ምንጩ ምንድነው ሲሉዋቸው እባካቹ ተውን ገገሩ ስም ይወጣል ከቤት ይቀበላል ጎረቤት ይላሉ። ኣሁንም እንደዚሁ ነው ነገሮች በደፈናው።

በመሆኑ የኢትዮጱያ ህዝቦች ሙሁሯኖች ይህ የጠባብነት ማእበል በንቃት መመልከቱ። በተለይ የትግራይ ህዝብና ሙሁራን ወላጆቻችን ከጥንት ጀምረው ለሁሉም ኢትዮጱያዊ ወነድሞቹ ግንባር ቀደምት ተሰልፎው የቀይባህርን ወራሪዎች በማንበርከክና መንኮታኮት ዘንት እለት እመከቱዋቸው ና እያጠቋቸው እንደመጡ ሁሉ ኣሁንም በባንዳዎች ሳንታለል ተጠንቅቀን ዘብ አንቁም !!!!!!!!!!!

ከኣስገደ ገብረስላሴ
ከመቀለ
11../02 / 2010

Share this post

One thought on “ህወሃት ትግራይን ለመገኝጠል መንደር ለመንደር እየተሽለኮለ የትግራይን ህዝብ እያነጋገረ ነው።

 1. (የትግራይ ጉዳይ…)” የኢትዮጵያ ህዝብ ነቅተህ ለሉኣላዊ ሀገርህና ለአንድነትህ ዘብ ቁም!!!!”– ከአሰገደ ገብረ ሥላሴ
  አንዳንድ ሸፍጥ አዘል መልሶች ይገርማሉ..አርጎት ነው!..ጥርግ ይበሉ!..ታላቋ ትግራይ በሃምሃሩ መቃብር ላይ አላሉም!ከኢትዮጵያ አንድነትና የክብር ኑሮ የኤርትራ ባርነት መርጠው ነውን? ብለው ያጎረመርሙ ጮክ ብሎ ይደመጣል።
  *******!
  የመጀመሪያው የሀገር ሉዓላዊነት የተደፈረው ወደብን አልፈልግም ብሎ ለአክስት ልጅ ሰጥቶ ፹ ሚሊየን ሕዝብ ፴፭ ከመቶ ዓመታዊ ባጀት የጥንት ወዳጅ ሀገር ጅቡቲን መጥቀምና ገንዝብ አለን ወደብ እንገዛላን ብሎ መሞላፈጥ ነው።በውስጠ ሚስጥሩ ግን አባት ሀገር ኤርትራ ጥቅም ከሚነካና ሕወሓት ዋናውን የሙስና መር ኢኮኖሚ ከሚያስነካ ቀላሉ ሻቢያን መንከባከብ ነበር።

  ቀጥሎ ከጎንደር ጫፍ እስከ ጋንቤላ ደረስ ፩ሺ ፪፻ ኪ/ሜ ለወዳጅ ሀገር ሱዳን በሹምባሽ አለቃ ጉዌን የተሰመረወን መስመር ተከተሉ “ሱዳን ባለፉት ነገስታትና ሀገር መሪዎች (ነፍጠኞች) የእናንተን እንካፈለ የእኛን አትንኩ እየተባሉ ለዘመናት አንገቱን ደፍቶ የኖረ ሕዝብ ነው” ለገሠ መለሰ የጠየቁትን መሬት ይሰጣቸው ሲል አወጀ…ከሰሜን ትግራይ ከመሐል ሀገር ለምን? ያለ አልነበረም ውጦ/ተውጦ ዝም አለ።

  እየተበደርንም እየተመፀወትን ለጎረቤት ሀገራት ሠላምና መረጋጋት መሐሉና ዳር አርገን እርስ በርስ በሜንጫ ሲተላለቅ፡ ተፈናቃይ፡ ቁስልከኛ፡ የእሬሳ ቆጠራ፡ ፉክክር በተለያዩ ቋንቋና ሚዲያ በማሳየት ደስተኞች ነበርን፡ የድሃ ልጅ ለሱማሊይና ደቡብ ሱዳን መረጋጋት የቦንብ አምካኝ በነጻ ማቅረብን እንደጀብዱ ሲቆጠር..ሲጀምርም የትግራይን ወጣት ለሻቢያ ነፍስ አድን በነጻ ለጦር ግንባር ያቀረብን..ዛሬም ገበሬና የጭን ገረድ ከትግራይ ለሻቢያ በማቅረብ የማታሸልበው ከተማ በኤርትራ ሙዚቃ አብዳ አደለምን!?

  ** እንግዲህ ግድብ ሞኝ ሠፈር..መብራት ጎረቤት ሀገር መንደር..ለጅቡቲ ንጹሕ ወሃ..ለኬንያ መብራት..ለሱዳን መብራትና ጥሬ እህል በልዋጩ የነዳጅ መቀጃ ባቡር ሐዲድ…ለግብጽ የቅናሽ መብራት አቅርቦት፡ተፋሳሽ ሀገራት መካከለኛው ምሥራቅና አውሮፓ መብራት ይሸጣል ድንፋታ’ሳይከካ ተቦካ’..መጀመሪያ ራስ ዳሸንን በመጽሐፍ በመዝረፍ፡ ጎንደርን በካርታ በመቁረጥ፡ ጎጃምን በቤንሻንጉል በመቀነስ ሕልመኛዋ ‘ታላቋ ትግራይ ትግሪኝ’ ወሎ፡ አፋር፡ጎንደር ተቀንጭቦ አሰብን በባቡር አገናኝቶ ከዝግ መሬት የወድብ ባለቤትነት ማግኛው ወቅት ደህንነቱን መከላከያውን ኢኮኖሚውን በአስተማማኝ ሁኔታ በብሔር ብሔረሰብ ቱማታ፡ አፍዝ አደንዝዝ፡ በበቂ ውጥንና በጥልቅ ራዕይ ተመስረቶ እንጂ የአንቀጽ ፴፱ ውጤት አደለም!። (የማስገነጠል አቅም ቢኖረው የህወሓት ትግራይ ደጋፊ የኢትዮ ሱማሊ ክልል ብቻ ድጋፍ ምንም የሚሆን ነገር የለም!)
  እሳት/ወላፈን/ነበልባል ብቻ ሳይሆን እረመጥ ያለው ከንቱ ልፋት።
  _____________!
  *፵፬ ዓመት ብቻ ሳይሆን ባንዳ/ሹምባሽ ‘ለጠላት ዶሮና እንቁላል ያቀረበ’እንደአሉት ክቡር ገብረመድክን አርዓያ ጥሊያንና እንግሊዝ ሚሽነሪስት ያወረሳቸው ንብረት ሳይሆን ተንኮልና ሌብነት ነወና ተጠራርተው/ተባብረው ሀገር አይበትኑም ማለት አይቻልም። ግን ነጻነት ወይስ ባርነት? ለመሆኑ ህወሓት ምን ጎድሎባት ሁሉን እያማሰለች ልገንጠል አለች!?ቢቻል ልዩ ጥቅማጥቅመኞችን በማቀያየር..ሆድ አደር..አድርባይ አውርቶ አደር፡ ሙሰኛን በክልል እያስፈለፈለች ተጠብቃ መኖር አዋጭ ንግድ አደለምን!? የትግራይ ፖለቲካ ተንታኝ እንዳለው “ክልሎችን በርከት ፌደራል ቋንቋቅውን ቁጥሩን በዛ ማድረግ መፍትሔ ነው።”አለ ባንዲራና ቋንቋ በበዛ ቁጥር ሜንጫ ይበዛል እነአጅሬዎች የበግ ለምድ የለበሱ ቀበሮዎች በአንድ ብሔራዊ ቋንቋና ዓላማ በማይግባባ ትውልድ የ፻ ዓመት የቤት ሥራቸውን በ፶ ዓመት ለማጠናቀቅ፡ የጀዘበ፡ወጣቱን ተንቀሳቃሽ ተናጋሪ እንስሣ አድርገው፡ በእየ ፲ ዓመቱ የመሃይም የሕዝብ ብዛቱን እየቆጠሩ ራዕዩ እያሻሻሉ ይቀጥላሉ። ለመሆኑ ኤርትራን አላስገነጥልም ያለው ለሰነደቀና ለሉዓላዊነት የሞተው የአማራ ትውልድ ምን አተረፈ?..ትምክተኛ፡ ነፍጠኛ፡ ጨቋኝ፡ ባሪያ አሳዳሪ፡እየተባለ እየተሳደደ/እየተሰደደም ይገደላል፡ ይፈናቀናል፡በእሳት ይቃጠላል፡ሰውነቱ ብሜንጫ ይተለተላል፡ አሁን ትግሬ አይገነጠልም!ቢል ምን ይባላል? ምን ሊያተርፍ ነው?ጥሪው መሆን ያለበት ኢትዮጵያዊ ትግሬ መንሳት አለበት…ወደ ወገኑ መፍለስም፡ መተባበርም፡ ማመጽም፡ በተለጣፊና ተምች የትግሪ መሰል ደናቁርት ምሁራንና ካድሬ፤ ሹምባሽ ላይ የማያዳግም ቅጣት ማሳየት የግድ ነው “ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም!”።በኢትዮጵያ በመከባበርና ትብስ ትብሽ አብሮ መኖር ከክፍለ ሀገር ወዳጅነትና ግንጠላ በላይ አኩሪ፡ጠንካራና አስተማማኝነት አለው። ሠላም ለሁሉም ሠላም ይሁን በቸር ይግጠመን!

  Reply

Post Comment