ህወሓት እንደ ራስ ሚካኤል ስሁል!!

Source: http://welkait.com/?p=12672
Print Friendly, PDF & Email

የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስቱ እጅግ ተዳክሞ በነበረበት በ18/19ኛው ክፍለ ዘመን ፓለቲካ የትግራዩ ሰው ንጉስ አንጋሽ ራስ ሚካኤል ስሁል በጎንደር መንገስ ሳያስፈልገው ይሆኑኛል ይጠቅሙኛል ያላቸውን ደካማ ልዑላን ወደመንበር እያወጣ ሲያወርዳቸው መኖሩን እናስታውሳለን።

ራስ ሚካኤል ጠንካራ ስብእና የነበረውን ልዑል በማንገስ ሀገሪቱ ከፓለቲካ ቀውስ ልትወጣ የምትችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይችል ነበር፤ ሆኖም ግን ጠንካራው ሲነግስ የብልጣብልጦች ዘመን ያከትማልና ራስ ሚካኤልም ታሪክ የፈጠረለትን የተደማጭነት እድል ራሱ መንገስ ሳያስፈልገው (ልዑላዊነት ስላልነበረው በዘመኑ መንገስ አይችልም ነበር) ለዚሁ ለግል የህይወት ዘመኑ መጠቀሚያ አድርጎት ታሪክም ዘግቦት አልፏል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ከጉራ ፈረዳ እና ከደቡብ ክልል እንዲባረሩ ያደረገው ሽፈራው ሽጉጤ

ዛሬ ህወሓት ለጠቅላይነቱ “ውድድር” እጩ አላቀረበችም ይህ ማለት ግን ስልጣኑን አልቁዋመጠችበትም ማለት አይደለም። ይልቁንም ህወሓት እንደ ራስ ሚካኤል ሁሉ መንገስ ሳያሻት የንጉስ አንጋሽነቱን ሚና በተጨባጭ ለመጫወት ወሳኝ 45 እጆችን ይዛ ስለምትገኝ ይሆነኛል ላለችውም ሰው ሲያሻት ሙሉ ድምፅ በመስጠት ካሻትም አብላጫውን ወይንም ገሚሱም በመስጠት ታነግሰዋለች፤ ይህን አደራ የሚበላ ሰው ግን ብዙ ቃል መግባት ይኖርበታ!!

ይህ ሚካኤል ስሁላዊ የፓለቲካ ምልሰት ነገ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሊያነግስ የማይችልበት ሁኔታ የለም። እኛም በፋንታችን ወይ ብአዴን ወይ ኦህዴድ እንላለን (የማናቸውም መንገስ የችግሮቻችን ፍፃሜ ሊሆን ባይችልም)። አንድ ነገር ግን መገንዘብ ያስፈልጋል ይሄውም የሀገሪቱ ዘመንኛ የፓለቲካ ችግር የአናሳ ፓለቲካ የወለደው መሆኑን። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች አናሳን የወከለ ወደ መንበር እየወጣ ሲወርድ ብዙሀኑን የወከለው በትዝብት የሚመለከትበት አጋጣሚ ከአንድ ወይም ከሁለት ግዜ የበለጠ ሊሆን አይችልም….የተፈጥሮው ህግ ይህን ያስገነዝበናል!!

On a related note, this is what Mr. Shigutie, former president of SNNPR, once said on a televised speech about defenseless Amhara of Guraferda district:

Amharas of Guraferda? Well, we have provided them with Isuzu cars so that they may soon leave our region and go back to where they come from.

I never for once read any official statement from ANDM calling this (and so many other similar acts) an act of ethnic cleansing.

The man is clearly a criminal by his deed, ANDM and the entire government by their silence!!
And here we stand now that this very person has 33.3 percent chance to be appointed as an interim premier.

ለካንስ ኢትዮጵያ የምር ትልቅ ሰው ጠፍቶብሻል!!
How sad!!

Belete Mola reports

የግርጌ ማስታወሻ
==========
ሽፈራው ሽጉጤ በጉራፈርዳ እና በሌሎች የደቡብ ክልል ዞኖች በመቶዎች ለሚቆጠሩ አማራዎች ግድያ እንዲሁም በ10 ሺህዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን መፈናቀል እና ንብረት መውደም ተጠያቂ የሆነ ሰው ነው።

ይህ ወንጀለኛ ለደህዴን ሊቀመንበርነት እና ለሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት መታጨት ሳይሆን ዘሄግ ላለው አለማቀፉ ፍርድ ቤት ቀርቦ የዕድሜ ልክ እስራት ማግኘት የነበረበት ሰው ነው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.