“ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር አልችልም” ያሉት ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ጠበቃቸውን አሰናበቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      መስከረም 6 ቀን 20…

“ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር አልችልም” ያሉት ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ጠበቃቸውን አሰናበቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 20…

“ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር አልችልም” ያሉት ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ጠበቃቸውን አሰናበቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የም/ቤት አባል አቶ ልደቱ አያሌው በደብረ ዘይት ወረዳ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። አቶ ልደቱ “እኔ የታሰርኩት ለምን ወንጀል ፈፀምክ ተብዬ ሳይሆን ለምን አሰብክ ተብዬ ነው” በማለት የክስ ሂደቱ የማሰብ ነጻነትን በመጋፋቱ ትክክል አለመሆኑ ጠቅሰዋል። አቶ ልደቱ ጠበቆችን ባሰናበቱበት ደብዳቤያቸው ካለፉት ስምንት የችሎት ሂደቶች “በፖለቲካ እና በህግ መካከል ክርክር እየተኪያሄደ መሆኑን እና ሁልጊዜም ግን በክርክሩ አሸናፊ እየሆነ ያለው ህግ ሳይሆን ፖለቲካ መሆኑን ነው።” መታዘባቸውን አስታውቀዋል። ሲቀጥሉም “ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር ስለማይቻል ከአሁን በኋላ ህጋዊ ግዴታዬን ለመወጣት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በችሎት ፊት ከመገኘት ባለፈ የህግ ክርክር የማድረግ ፍላጎት የለኝም።” ሲሉም አስፍረዋል። “ስለሆነም እስከአሁን ለሰጣችሁኝ ልባዊ አገልግሎት ምስጋናዬን እያቀረብኩ ከዚህ በኋላ ግን ትርጉም የሌለው የህግ ክርክር በማካሄድ የእናንተን ውድ ጊዜ ማባከን ስለሌለብኝ የጥብቅና አገልግሎታችሁን ማግኘት የማልፈልግ መሆኑን በአክብሮት እገልፃለሁ።” ሲሉ ነው ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴንንና የሙያ ባልደረቦቻቸውን ያሰናበቱት። የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ከአሁን ቀደም ለጠ/ሚ አብይ አህመድ በጻፉት ደብዳቤ “የአርቲስት ሀጫሉን ሞት ተከትሎ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የብሄራዊ ምክር ቤት አባላቸው አቶ ልደቱ አያሌው ለእስር መዳረጉ እንዳሳዘናቸው ገልፀው “ፓርቲያችንም ሆነ አቶ ልደቱ በሰላማዊ ትግል ላይ ያላቸው የማያወላውል አቋም በግልፅ እየታወቀ አቶ ልደቱን በብጥብጥ እና ሁከት አሳቦ ማሰር የሚያሳየው ፓርቲያችንን ለማዳካም ሆን ተብሎ እየተሰራ መሆኑን ነው፡፡” ሲሉ ማስፈራቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply