ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ፣ጸሎትና ምሕላ ታወጀ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79805

ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ፣ጸሎትና ምሕላ ታወጀ፡፡

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየ ዕምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ፣ጸሎትና ምሕላ እንዲያደርጉ ታወጀ፡፡
የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች እና የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች አሁን በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጉባኤው የወገኖቻችን ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት በአፋጣኝ በማቆም ሁሉም ወገን ቅድሚያ ለሀገራዊ አንድነት ፣ለሰብአዊ ክብርና ሰላም ሊተጋ ይገባል ሲሉ የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከዚህ በኋላም በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ምንም አይነት ግጭት እና የሚተኮስ ጥይት ሊኖር እንደማይገባም አሳስበው፤ኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጋራ በመሆን ለመላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባለአስር ነጥብ የሰላም መልዕክት እና የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ግጭቱ ተወግዶ የታሰበው ሰላም እውን እንዲሆንም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየ ዕምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ጸሎትና ምሕላ ታውጇል ብሏል ጉባኤው፡፡
 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.