ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ ሊሰጥ ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/148883

BBC Amharic
የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በያዝነው አዲሱ 2012 ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1148/2011 መሰረት፤ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን የቴሌኮም ዘርፉን በመቆጣጠር በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ተቋማት የውድድር ገብያውን ምቹ ለማድረግ የተቋቋመ ነው።
አቶ ባልቻ ሬባም ተቋሙን ከያዝነው አዲስ ዓመት ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሹመዋል።
“ይህ ተቋም በዚህ ዓመት ለመፈጸም ካቀዳቸው ዋና ተልዕኮዎች መካከል፤ ለሁለት በቴሌ-ኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ለሚሰሩ ተቋማት ፍቃድ መስጠት ነው” በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።
መንግሥት ከዚህ በፊት 51 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ በእራሱ ሥር አቆይቶ 49 በመቶውን ደግሞ ወደ ግል ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ማስታወቁ ይታወሳል።
የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት የቴሌኮም ዘረፉ ለግል ድርጅቶች ክፍት እንደሚደረግ ይፋ ካደረገ በኋላ በርካታ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ገብያ ላይ ፍላጎት ሲያሳድሩ ቆይተዋል።
“ከስድስት ወራት በኋላ ፍቃድ ወደመስጠቱ ሥራ እንገባለን” የሚሉት አቶ ባልቻ የአውሮፓውያኑ 2019 ከመጠናቀቁ በፊት የቴሌኮሚኒኬሽን ኦፕሬሽን ፍቃድ ይሰጣል ተብሎ ነበር ይላሉ።
ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሉት ከሆነ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ፍላጎት ያላቸው ተቋማት የንግድ ሃሳባቸውን እንዲያስገቡ በጠየቀው መሰረት ገቢ ያደረጉ ተቋማት አሉ ብለዋል።
”የቴሌኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ፍቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት የውጪ ሃገር፣ የሃገር ውስጥ ወይም በሽርክና የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ” ብለዋል።
ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሆነው ይህ ባለስልጣን ያልተገቡ የገበያ

Share this post

One thought on “ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ ሊሰጥ ነው

  1. The exact content of this news is what is posted by BBC in Afan Oromoo. The director general did not say “proposal submission is already requested and proposals are submitted.” What he said is so far no proposal is submitted, and proposals will be submitted after the Authority announces for submission.

    Correct your translation.

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.