ለማ መገርሳ የሀገርና የህዝብ ባለውለታ ነው ! – አበጋዝ ወንድሙ

ባለፈው ሳምንት፣ የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታና በፓርቲው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። ስብሰባው ሲጠናቀቅ በክልሉ ውስጥ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ፣ በዜጎች ላይ ብሄር ወይንም ሃይማኖት ተኮር የሆኑ እጅግ አሳዛኝ ግድያዎችና አካላዊ ጥቃቶች፣መፈናቀሎች ፣ የግለሰቦች ንብረት ውድመትና፣ እጅግ የከፋ የከተሞች ውድመትን አስመልክቶ ስላደረገው ውይይትም ሆነ  ችግሩንም በጊዜያውነትም ሆነ በዘላቂነት ለመቅረፍ ያሳለፈው ይሄ ነው የሚባል ውሳኔ አልሰማንም። ይልቁንም በስብሰባው መጨረሻና ከዛ በዃላ በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲም ሆነ በዜና አውታሮች የመወያያ ርዕስ ሆኖ የከረመው፣ በሶስት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የብልጽግና ፓርቲ ወሰድኩ ያለው፣ ከድርጅቱ አመራርነት የማገድ ተግባር  ነው። እግድ ከተጣለባቸው ሶስት የአመራር አባላት አንዱ ለማ  መገርሳ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply