ለሩት ቤደር ጊንስበርግ የጸሎትና የአክብሮት ሥነ ስርዓት

https://gdb.voanews.com/42204B12-A50D-4490-991C-BF1E24FBEB7F_w800_h450.jpg

ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ የጸሎትና የአክብሮት ሥነ ስርዓት እየተካሄደ ነው።

የዳኛ ጊንስበርግ አስከሬን ዛሬ ጠዋት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተወስደ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ባልደረቦቻቸውና በተገኙበት የጸሎት ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ አስከሬን በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋናው መግቢያ በር ደጃፉ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ህዝቡ ዛሬና ነገ አክብሮቱን እየገለጸ ይሰናበታል።

ከነገ በስቲያ ዓርብ ወደዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ካፒቶል ተወስዶ በክብር እንደሚያርፍና የተጠሩ እንግዶች የሚገኙበት የጸሎትና ስንብት ሥነ ስርዓት ከተከናወነ በኋላ ህዝብ እየተሰናበተ የሚያልፍበት ዝግጅት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በሰማኒያ ሰባት ዓመታቸው ያረፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ የቀብር ሥነ ስርዓት የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲና ወንድሞቻቸው፣ ስመ ጥር ሴኔተሮች ሮበርት እና ኤድዋርድ ኪኔዲ እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መቃብር በሚገኝበት በአርሊንግተን መካነ መቃብር በሚቀጥለው ሳምንት ይከናወናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply