ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ እስከ አሁን 1 ሚሊየን 394 ሺህ 922 ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸው ተገለፀ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%88%88%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A0-%E1%8B%8D%E1%88%B3%E1%8A%94-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8A%A8-%E1%8A%A0%E1%88%81%E1%8A%95-1-%E1%88%9A%E1%88%8A%E1%8B%A8%E1%8A%95-394/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ እስከአሁን 1 ሚሊየን 394 ሺህ 922 ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የቦርዱ ስራ ሃላፊዎች እና የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ አባላት በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው የምዝገባ ሂደቱን በዛሬው ዕለት ተመልክተዋል፡፡

በ1 ሺህ 692 የምዝገባ ጣቢያዎች ብዛት እስከ አሁን 1 ሚሊየን 394 ሺህ 922 ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን ያስታወቀው ቦርዱ በሃዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ምርጫ ጣቢያ አካባቢ አንድ ቀላል ሁከት ማጋጠሙን ገልጿል፡፡

ይህም በምሽት ወደምርጫ ጣቢያ ተጠግተው የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የሃዋሳ ከተማ ፓሊስ የዝፊያ ሙከራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከፍተኛ ተመዝጋቢ የታየባቸው አካባቢዎች- አርቤጎና፣ ሁላ፣ ወንሾ እና ቦና ዙሪያ እንዲሁም ዝቅተኛ ተመዝጋቢ የታየባቸው አካባቢዎች ሃዋሳ ከተማ፣ አለታ ወንዶ እና ዳራ ናቸው ተብሏል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.