ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ መጀመሩ ተገለፀ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%88%88%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A0-%E1%8B%8D%E1%88%B3%E1%8A%94-%E1%8B%A8%E1%8B%B5%E1%88%9D%E1%8C%BD-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8C%AB-%E1%8A%AE%E1%88%AE%E1%8C%86%E1%8B%8E/

አዲስ አባበ፣ ህዳር 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዳር 10 ለሚደረገዉ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ መራጮች በሰላማዊ መልኩ ለድምፅ መስጫ የሚሆናቸውን ካርድ እየወሰዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት እስከዛሬ ሁለት ሚሊየን መራጮች ካርድ ወስደዋል፡፡

በአንዳንድ ቦዎታች ሶስት ቀናት የመራጮች ቁጥር በመብዛቱና ተጠባባቂ ካርድ በወቅቱ ባለመድረሱ የካርድ እጥረት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራ ምርጫ ቦርድ ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ካርድና በተጨማሪም መጠባበቂያ ማዘጋጀቱን ወይዘሪት ሶሊያና ገልፀዋል፡፡

የህዝበ ውሳኔዉ ቀነ ቀጠሮ ህዳር 10 ሳይደርስ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ተጓጉዘዉ እንዲያልቁ ከወዲሁ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ለህዝበ ውሳኔዉ ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ወደ በ1 ሺህ 692 የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁሶቹ በመጓጓዝ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በድምፅ መስጫዉ ቀን መራጮች የሚበዙበት ጣቢያ ካጋጠመ ቦርዱ ይህንን ከግንዘቤ በመውሰድ ተጨማሪ ድምፅ መሽጫ ጣቢያ ሊያቋቁም እንደሚችልም ወይዘሪት ሶሊያና ጠቁመዋል፡፡

ጌታቸዉ ሙለታ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.