ለአማራ ተጋድሎ የገንዘብ እርዳታ ! በቀጥታ የአማራ ሕዝብ ከዘረኛው ወያኔ ጋር እያደረገ ላለው ትግል የሚውል !!!

Source: http://moreshinfo.com/archives/3585

 

ለአማራ ተጋድሎ የገንዘብ እርዳታ – በቀጥታ የአማራ ህዝብ ከዘረኛው ወያኔ ጋር እያደረገ ላለው ትግል የሚውል

 

ዐማራውን ኅልውና አስጠብቆ፣ የዘረኛውን የወያኔን አገዛዝ በማስወደግ፣ አንድነቷ የጠነከረ፣ ሰላሟ የተሟላ፣ ዕድገቷ የተፋጠነ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ፣ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት እንደሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል። ለዚህም ለታሠሩ፣ ለተፈናቀሉ፣ ለተገደሉና በወያኔ እየተሳደዱ ላሉ የዐማራው ልጆች የሚያስፈልጋቸውን እገዛና ድጋፍ በውጭ የሚኖረው ዐማራና የዐማራው ወዳጅ የሆነ ሁሉ፣ በቀና መንፈስ ወገንን ከጥፋት የመታደግ ጥረት የበኩሉን እርብርብ ሊያደርግ ይገባል። ዛሬ በወያኔ ለተጎዱ ወገኖ የምንሰጠው ድጋፍ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን በቆራጥነት ለተያያዙት ወገኖች የሞራል ስንቅ በመሆን የሚያገልግል ከመሆኑም በላይ፣ ትግሉን ለድል እንዲበቃ ጋንን በጠጠር የመደገፍ ያህል ነውና፣ የዐማራው ልጅ፣ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በአክብሮት ጥሪ ያቀርባል። ዐማራው ለወገኖቹ የሚሰነዝረው የድጋፍ እጁ ከሚፈለገው ቦታ እንዲደርስ ለማድረግ ሞረሽ ወገኔ የበኩሉን ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ፣ ተጎጂ ወገኖቻችን ለመርዳት ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች በየምትኖሩበት አካባቢ ላሉ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበራት፣ ወይም በእንሂድ እንደግፍ (GO FUND ME ወይም በቼክ፣ በፔይ ፓል  መርዳት የሚቻልበትን መንገዶች አመቻችቷል።

ዛሬ ለወገናችን ማድረግ የምንችለውን ነገር ሳናደርግ ቀርተን፣ እንቅስቃሴው ቢገታ ፀፀቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ በልጆቻችን ተወቃሽ የሚያደርገን ስለሚሆን፣ የምንችለውን ያህል እጃችን ለወገናችን እንድንዘረጋ ግፍ በሚፈጸምባቸው ወገኖቻችን ስም ጥሪአችን እናቀርባለን!

በቀጥታ እርዳታ ለማድርገ የሚከተለውን ሊንክ ላይ በመጫን መርዳት ይቻላል።

https://www.gofundme.com/leamarategadlo-humanitarian-support

የወገናችሁ ስቃይና ሰቆቃ የእኛም ሰቆቃ ነው፣ የአማራ ህዝብ እያደረገ ያለው ትግልም የእኛም ትግል ነው በማለት የምትችሉትን ማንኛውንም እርዳታ እያደረጋችሁ ውድ የአማራ ልጆች ከልብ እናመሰግናለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.