ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና

Source: https://mereja.com/amharic/v2/46061

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና*
ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ
መግቢያ
በአንድ አገር ውስጥ የተሻለና አመኔታ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመመሥረት ነፃ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖር በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው። ነፃ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥትን የሚቆጣጠሩ፣ በዓይነ ቁራኛ የሚጠብቁ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸውና በአገሪቷ ህግ ዕውቅና ያላቸው ድርጅቶች ናቸው። ዋና ተግባራቸውም የመንግሥትን ተቋም በምርጫ አሸንፈው የሚመሩ፣ ለመንግሥት ሥልጣን ብቃት ያላቸው አባላትን በመመልመል ከመንግሥት ወይም ከገዢው ፓርቲ በልዩ ልዩ መስክ የተሻለና የበለጠ ፖሊሲ አለን፣ በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ተወዳድረን የመራጩን ህዝብ አመኔታ አግኝተን በመመረጥ ፖሊሲያችንን በተግባር እናውላለን፤ የአገሪቱ ህዝብም በዚህ ፖሊሲ ተጠቃሚ ይሆናል ብለው የሚንቀሳቀሱ ናቸው።
እነኚህ ፓርቲዎች የጠቅላላው ህብረተሰብ ነፀብራቅ ሲሆኑ፣ የፓርቲ ድርጅታቸውም በብቃት ሥራውን የሚያከናውን፣

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.