ለእሬቻ በዓል 5 ገንዳዎች ውሐ ተሞልተው የተዘጋጁ ሲሆን 50 ቦቴዎች ተሳትፈዋል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/154557

በመስቀል አደባባይ በነገው ዕለት ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የዋዜማ በዓል ዝግጅት እየተደረገ ነው
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በመስቀል አደባባይ በነገው ዕለት ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የዋዜማ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደበባይ በሚከበረው በኢሬቻ በዓል ዝግጅት ዙሪያ ፋና ብሮድካስቲንግ በአከባቢው ቅኝት አድርጓል፡፡

የበዓሉ ዋዜማ በዛሬው ዕለት 8፡ 00 ሰዓት ላይ የዋዜማ ፕሮግራም ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃለ፡፡
በዋዜማው ምሽት የህፃናት መዝሙሮች፣ የሙዚቃ ድግሶች እና ሌሎች ባህላዊ ትውፊቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
መስቀል አደበባይ ላይ ሁለት ገንዳወች ታጥበው ውሃ ተሞልተው ለበዓሉ ተዘጋጅተዋል፤ ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ የአፍሪካ ኢኖሚክ ኮሚሽን ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሶስት የውሃ ገንዳዎች ታጥበው በውሃ ተሞልተዋል፡፡
ለዚሁ አገልገሎት 50 ያህል የውሃ ቦቲ ተሸክርካሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ከከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ የአፍሪካ ኢኖሚክ ኮሚሽን ፓርክ ውስጥ በሚከናዎነው ስነ ስርዓት ላይ አበገዳዎች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጨምሮ በርካታ የበዓሉ ተሳታፊዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃ፡፡
በዚህ ወቅት መጨናነቅ እንደይፈጠር እንግዶቹ ለማስተናገድ መግቢያና መውጫ በሮች ተለይተዋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አቅጣጫ ወደ ፓርኩ ለመግባት የሚያስችሉ ሁለት በሮች ተዘጋጅተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ በበዓሉ ስነ ስርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ ለመውጣት በስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ ያለውን መውጭ መጠቀም እንዳለባቸው ነው የተገለጸው፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ከነገ በስቲያ ደብረዘይት ቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዲ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ተመሳሳይ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ነው የጣቢያችን ባልደረባ ሃይለሚካኤል ደቢሳ ከደብረ ዘይት የዘገባው፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.