ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/169020

(ስዩም ተሾመ)
ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው!!
ብሔርተኛ ሲባል “ራስ ወዳድ ጥቅመኛ ነው” የምላችሁ ለዚህ እኮ ነው። በአርከበ ዕቁባይ ዘመን የትግሬ ብሔርተኛ ከትግራይ ትምህርት ቢሮ ነቅሎ መጥቶ አዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ ከተሰገሰገ በኋላ የከተማውን ነዋሪ ግጦት ሄደ።  በታከለ ኡማ ዘመን ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች መልሶ ለመጋጥ እንዲህ አሰፍስፏል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ላይ “የታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝ” እንደ መስፈርት ተቀምጧል።
ከታች በምስሉ ላይ ያለው በኦሮምኛ የተፃፈ መልዕክት በተጠቀሰው ክፍት የሥራ ቦታ ለሚያመለክቱ የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ለማደል በስልክ ቁጥር 0921879712 ላይ እንዲደውሉ ጥቆማ ይሰጣል። የዚህን ስልክ ባለቤት ጨምሮ በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ ካልሆኑ ከከንቲባ ፅ/ቤት እስከ ቀበሌ ድረስ እየተሰራ ያለው ወያኔን ለመተካት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ በሚስጥር ሲተላለፍ የነበረው መልዕክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።
************************************************
No photo description available.የአ/አ (የፊንፊኔ ) ከተማ አስተዳደር በሁሉም የትምህርት መስክ አምስት ሺህ ሰዎችን አወዳድሮ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሥራ ማስታወቂያ በማውጣት ገልጿል፣

የምዝገባ ቀን 2/3/2012
መመዝገቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ
አስፈላጊ መመዘኛዎች
— በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ
— በ2010 እና 2011የተመረቃችሁ ብቻ
— የሥራ ልምድ 0 ዓሠት
አንድ ተወዳዳሪ ይዞ መገኘት ያለበት
የ10ኛና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
የ8: 10 12ኛ ክፍሎች ካርድ ኦርጅናልና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.