‹‹ለውጡን ለመቀልበስ በመካከላችን የተፈጠረውን እሳት በጥንቃቄ በማጥፋት የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መሠረት ያደረጉ ሥራዎቻችን እንጀምራለን፡፡›› አርበኛ ታጋይ መሳፍንት ተስፉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77605

‹‹ለውጡን ለመቀልበስ በመካከላችን የተፈጠረውን እሳት በጥንቃቄ በማጥፋት የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መሠረት ያደረጉ ሥራዎቻችን እንጀምራለን፡፡›› አርበኛ ታጋይ መሳፍንት ተስፉ

‹‹የተሳሳቱ እየተመከሩ፤ ያጠፉ በሕግ እየተጠየቁ ለኢትዮጵያዊነት ዋልታ የሆነ አንድ ታላቅ አማራን እንገነባለን፡፡›› ታጋይ ስጦታው ዳኘ (ባሻ)
በታጋይ መሳፍንት ተስፉ እና በታጋይ ስጦታው ዳኘ የሚመሩ 250 የሚደርሱ ታጋዮች  በዓፄ ቴዎድሮስ ስታዲዮም የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ስታዲዮም ለተገኘው ሕዝብ ንግግር ያደረጉት ታጋዮቹ አማራጭ ካልጠፋ በስተቀር ግጭት መፍትሔ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡
‹‹በታደጋጋሚ ጊዜ መታሠራችንና ሠርተን መብላት እንዳንችል መደረጉ ሳያንስ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ፣ ሀብታችን፣ ንብረታችን እና ቤተሰቦቻችንን ትተን ጫካ እንድንገባ አስገድዶናል›› ብለዋል ታጋይ መሳፍንት፡፡ ‹‹አሁን ከውጭ እኛና እናንተ በጋራ፣ ከውስጥ የለውጥ አመራሮቹ ባደረግነው የጋራ ትግል እንዲህ ለመገናኘት በመብቃታችን ደስ ብሎኛል›› ብለዋል በስዲታዮም ለተገኘው ሕዝብ፡፡
በተገኘው አንጻራዊ ሰላም መዘናጋት ሳይኖር የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መሠረት ላደረገ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መታገላቸውን እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡ ታጋይ መሳፍንት ‹‹ለውጡን ለመቀልበስ በመካከላችን የተፈጠረውን እሳት በጥንቃቄ ማጥፋት ይኖርብናል›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡
‹‹ላለፉት 27 ዓመታት ሕዝባችን የከፋ የመከራ ዘመን አሳልፏል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ከውጭ ያሉ ብቻ ሳይሆን ከውስጣችንም አሳልፎ የሚሰጥ ነበር›› ያሉት ታጋይ ስጦታው ዳኘ (ባሻ) የተሳሳቱት እየተመከሩ ያጠፉት በሕግ እየተጠየቁ ለኢትዮጵያዊነት ዋልታ የሆነ አንድ ታላቅ አማራን በጋራ ለመፍጠር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶችን እና በቦታው የተገኙ አካላትን ወክሎ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.