ለውጥ እንዲመጣ በሚል ለ3 ዓመታት ታስሮ በህዝብ ተጋድሎ የተፈታው ሰጠኝ ቢልልኝ ዛሬም በጎንደር ከተፈፀመበት የሰዓታት እስር ቆይታ በኋላ መፈታቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከ…

ለውጥ እንዲመጣ በሚል ለ3 ዓመታት ታስሮ በህዝብ ተጋድሎ የተፈታው ሰጠኝ ቢልልኝ ዛሬም በጎንደር ከተፈፀመበት የሰዓታት እስር ቆይታ በኋላ መፈታቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከ…

ለውጥ እንዲመጣ በሚል ለ3 ዓመታት ታስሮ በህዝብ ተጋድሎ የተፈታው ሰጠኝ ቢልልኝ ዛሬም በጎንደር ከተፈፀመበት የሰዓታት እስር ቆይታ በኋላ መፈታቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ ነዋሪና በተፈጥሮ ሀብት ባለሙያነት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሰጠኝ ቢልልኝ የትህነግ መራሹን ስርዓት አስተሳሰብና አካሄድ ባለመቀበላቸው በግፍ ታስረው ከተሰቃዩት መካከል ይጠቀሳል። ትህነግ በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፅመው የነበረውን ተደጋጋሚ ግፍና በደል ለምን ብሎ በመጠየቁ፣ በማውገዙና በመታገሉ በስርዓቱ ካድሪዎች ጥርስ ተነክሶበት ከ2007 እስከ 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ፣ዝዋይና ሸዋሮቢት ተወስዶ በእስር ከፍተኛ ዋጋ የከፈለና በህዝብ ተጋድሎ ከተፈቱት የአማራ ታጋዮች መካከል አንዱ ነው። ሰጠኝ ቢልልኝ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ትብብር ለአካል ጉዳተኞች ህይወት ማቋቋሚያ ማህበር (ትጉህ) ቢሮ ውስጥ ባለበት በደህንነትና በፖሊስ አባላት እስርና ወከባ የደረሰበት መሆኑ ተገልጧል። ጎንደር በሚገኘው የትጉህ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚሰራበት ነው የደህንነት እና የፀጥታ አካላት ቢሮ ውስጥ በመግባት በክልል ደረጃ እውቅና አግኝቶ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተንቀሳቀሰ ያለን ማህበር ህገወጥ ነው በሚል ለእስር የዳረጉት። ይሁን እንጅ ከሰዓታት በጎንደር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የእስር ቆይታ በኋላ በትጉህ ፕሬዝዳንት በመ/ር ጌታ አስራደ በኩል በተደረገው ጥረትና ማህበሩ እውቅና ያለው መሆኑ ተነግሯቸው መፈታቱን ነው ሰጠኝ ቢልልኝ ያስታወቀው። እስሩ ሆንተብሎ ለማሸማቀቅ ብቻ ሳይሆን በህወሀት አምባገነን ስርዓት ዋጋ የከፈሉ ተጎጅዎች እንዲበተኑ ከመፈለግ የመነጨ ነው ብሎ እንደሚያምንም ገልጧል። ከአሁን ቀደም በኢትዮ 360 ላይ መንግስት ተጎጅዎችን ለማቋቋም አልቻለም ብሎ የወቀሰበት ንግግሩም ተጠቅሶ የተጠየቀ መሆኑን አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ስለደረሰበት እስርና የትጉህ ማህበር እንቅስቃሴ ጉዳይ ከሰጠኝ ቢልልኝ ጋር ቆይታ አድርጓል። በአሚማ/AMC የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply