ለዕንቁው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ጌታቸው ረዳ ዘብሔረ – አክሱም!

Source: http://welkait.com/?p=11435
Print Friendly, PDF & Email

ከሁሉ በተቀዳሚ የተከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ከነመላ ቤተሰብዎ ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በደስታ አደረሰዎ እንላለን።

በመቀጠልም ዛሬ ሰው ጠፍቶ አገራችን በባንዶችና ቅጥረኞች ተዋናይነት በታሪካዊ ጠላቶቻችን አቀነባባሪነትና ድጋፍ በጥፋት ዋዜማ ላይ በምተገኝበት ወቅት እርስዎና ሌላው ስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ የትግራይ ተወላጅ ክቡር አቶ ገብረመድኅን አርያ ዘወትር ያለማሰለስ ላደረጋችሁት እና ለምታደርጉት ተጋድሎ ከፍተኛ ምስጋናችን እናቀርባለን። በርቱ በርቱ!!

Getachew Reda Author and Editor of Ethiopian Semay website still stand against all odds!

ሰሞኑን አንዳንድ እራሳቸውን ኢሕአፓ ባይ አወናባጆች ሁሉ ከተወሸቁበት ጠባብ ጉረኖ ብቅ እያሉ ሐቁ ሲነገርና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ሴራቸው በተጨባጭ ማስረጃ ሲጋለጥ ልክ እንደ እብድ ውሻ ያቅነዘንዛቸዋል። እነዚህ ሕሊናቢስ ጉዶች በራሳቸው ስምና ማንነት በሠለጠነ መንገድ በአደባባይ ወጥተው የሃሳብ ክርክር ማድረግ የማይችሉት በጣም ዝቅተኛ ፍጠረቶች፣ በመሳደብና ውሸትን ቆርጦ በመቀጠል ሌላውን ዝም ለማሰኘት የሚያደርጉት ከንቱ ድርጊታቸው ከሽፎባቸዋል። …… (ሙሉውን ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ)

Share this post

One thought on “ለዕንቁው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ጌታቸው ረዳ ዘብሔረ – አክሱም!

 1. የተከበሩ ዶ/ር ጌታቸው ረዳ(ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)
  “ከሁሉ በተቀዳሚ የተከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ከነመላ ቤተሰብዎ ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በደስታ አደረሰዎ እንላለን። በመቀጠልም ዛሬ ሰው ጠፍቶ አገራችን በባንዶችና ቅጥረኞች ተዋናይነት በታሪካዊ ጠላቶቻችን አቀነባባሪነትና ድጋፍ በጥፋት ዋዜማ ላይ በምተገኝበት ወቅት እርስዎና ሌላው ስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ የትግራይ ተወላጅ ክቡር አቶ ገብረመድክን አርዓያ….ስለመልካም ሥራችሁ ቁርጠኝነትና እውነተኝነታችሁ እናመግናለን።በርቱ!

  “ጅብ በማያቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” አለ ሌሊቱን ሲቆረጥም ሊያድር እንኝህ ምግባረ ብልሹ፡ የትወልድ ፀሮች፡ የሚኢሶንና ኢህአፓ ደናቁርት ትውልድ በልተውና አባልተው ብቻ ሳይሆን፡ ዘመን ጨርሰውም፡ ዛሬም ባለጌ አፋቸው ጭቃ ጭንቀላታቸው፡ መልካም ሥም ከማጉደፍ ሰው ከመዘርጠጥ፡ ከዛቻና ባዶ ፉከራ አልታቀቡም ያው የደም ጥማት ያቃዣቸዋል፡ “አንተ ትግሬ ነህ ለአማራው ማን ወከለህ?” የሚሉ ጡሩበኞችና ጭንጋፎች፡ ለመሆኑ እነሱ ማን ወክሉኝ ብሏቸው ነው? እነሱስ ማን ቢሆኑ ነው? አማራው በመኢሶንና ኢህአፓ እንዲጠረነፍ እንዴት ተፈረደበት? ዋለልኝ የወሎ ወላዋይ (የተለባ ሥፍር) ስለሆነ(ኑ) አልቀረባቸውም።
  ድንቄም! ብሔር፫ ብሔረሰብ፪ እና ሕዝቦች፩…. አባቷን አታቅ አያቷን ናፈቅ!

  ** በተሃድሶ(አጋልጥ) ወገናቸውን እህት ወንድሞቻቸውን ለደርግ ሰው በላ አልሞ ገዳይ፡ ገራፊ፡ ጥፍር ነቃይ፡ በጋዜጣ ብልት አቃጣይ፡ ጭዳ ብለው አውሮፓ፡ አሜሪካና ሶሺያሊስት ሀገር ተሸጉጠው፡ ትናንት ለደርግ ያፈነደዱ፡ ዛሬም ለህወሓት/ኢህአዴግ ቀንደኛ አማካሪ/ያጎበደዱ ፡ በቀለኞች፡ በሀገር ማጥፋት ተሳታፊዎች፡ የዲያስፐር የወሬ ኢንቨስተር ውክልና አግኝተው የሚቀሳፍቱ ‘ጥርቅምቅም ድናቁርት’ ኩሩ፡ሀገር ወዳድ፡ ንፁሕ ግለስቦችን ለመተናኮል እጃቸው ያለበት ሁሉ አዎን! አርፈው ቢቀመጡ ይሻላል። ልጅ “እናትህ የት ሄደች ቢሉት ያላዩባትን ልታወራ” አለ አሉ
  ለነገሩ ጌታቸው ረዳ ዋዛ አደሉም፡ በኮረኮሯቸው ቁጥር ታሪካቸውን እንደቆፍጣና ገበሬ መንሽ ጉዳቸውን ለንፋስ ይበትኑላቸዋል፡፡ ድሮስ… የሰው ልክ የማያወቅ ባለጌ ትርፉ ይኸው ነው ባትሉኝ… እያረጁ ጥሬ በለው!

  የኢትዮጵያ ጥናት ማኅበር ምርምር ዘርፍ አባለት ሁሉ ፤ስለመልካም እይታና ጥበቃችሁ እናመሠግናለን!።በርቱ!በርቱ!
  በቸር ይግጠመን

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.