ለጀግነዋ እህታችን ለንግስት ይርጋ የተገተመች ግጥም!

Source: http://welkait.com/?p=12353
Print Friendly, PDF & Email

ንግስቴ ነሽ አንች
•••••••••••••••••••

ንግስትን አግኝቸ ደመቀልኝ ቀኔ፣
ደስ ብሎኛል ዛሬ እልል በል ወገኔ።

የጀግና መስፈሪያ ታሪክ ያ ደመቀ፣
እጅ አልሰጥም ብሎ ገዳይ ያስጨነቀ።

ንግስትን ስፈልግ ስባዝን ስለፋ፣
በደመቀ ቀኔ ዛሬ ታየ ተስፋ።

እኔ አልተሳሳትኩም እንችን በመውደዴ፣
ያገኝሁሽ ለታ ደመቀልኝ ዘውዴ።

ፍልቅልቋ ጀግና የአማራ ምልክት፣
ዳግማዊ ጣይቱ አንች እኮ ነሽ ንግስት።

@ሰጡ ብርሃን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.