ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸው የተባሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/119736

በቤኔሻንጉል ጉሙዝና አካባቢው ‹‹ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸው›› የተባሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው በቤኔሻንጉል ጉሙዝና አካባቢው ‹‹ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸው›› ተብለው የተጠረጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ተግባር እንደቀጠለ ነው፡፡
የማንዱራ ወረዳ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉጎጃም አማረ እና የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አረጋ ትናንት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል፡፡በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ ደግሞ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታው ሽመልስ እና የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ካሳ ድረስ ትናንት በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት በአካባቢው ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንና ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩ ይታወቃል፡፡ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንቻ አምሳያ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋህ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡- አብመድ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.