ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄ የቀረበው ከኦሮሚያና ደቡብ ክልል ብቻ ነው – ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77835

ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄ የቀረበው ከኦሮሚያና ደቡብ ክልል ብቻ ነው -የፌዴሬሽን ምክር ቤት
በአሁኑ ወቅት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄ የቀረበው ከሁለት ክልሎች ብቻ መሆኑን አፈ ጉባዔ ኬሪያ ኢብራሂም ገለጹ።ምክር ቤቱ በማንነት ጉዳዮችና የጥያቄዎች አፈታት ላይ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ነው።በስልጠና መድረኩ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንደተናገሩት፤ የማንነቴ ይታወቅልኝ ጥያቄዎች የቀረበው ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ነው።

በኦሮሚያ ክልል የማንነቴ ይታወቅልኝ ጥያቄ ያቀረቡት የዛይና የጋሮ ማህበረሰቦች ሲሆኑ፤ ከደቡብ ክልል ደግሞ የዶርዜ፣ የቁጫና የወለኔ ማህበረሰቦች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።”ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህገ-መንግስቱ በተሰጠን ስልጣን መሰረት ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት ጥያቄ የቀረበለት ከሁለቱ ክልሎች ብቻ እንደሆነ ቢገልጽም፤ በተለያዩ ክልሎች የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ” ጥያቄዎች እየተነሱ ግጭቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል።የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከዚህ ቀደም ጥቅምት አጋማሽ ላይ ለ13ኛ ጊዜ ለሚከበረው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡት ወቅት የማንነት ጥያቄ ሲቀርብ ስርዓትና ህገ መንግሰቱን መሰረት አድርጎ መጠየቅ፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድም መመለስ እንዳለበት ገልጸዋል።
የማንነት ጥያቄ የሚያነሳ አካል መጀመሪያ ለወረዳ፣ ለክልል፣ ከዚያም ክልል ካልመለሰው ደግሞ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በይግባኝ መልኩ ማቅረብ እንዳለበት መናገራቸውም ይታወሳል።በወቅቱም የወልቃይት ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ‘የአማራ ማንነት’ ጥያቄ ይዘው መምጣታቸውንና ምክር ቤቱም ጥያቄው በክልል ማለፍ እንዳለበት ገልጾ ምላሽ መስጠቱን እንዲሁም የራያ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.