ለ2012 የኢትዮጵያዊያን አዲስ ዓመት ከተደመረው ኢሕአፓ የተሰጠ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/145832

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ ሕ አ ፓ )
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP)
No photo description available.ለ2012 የኢትዮጵያዊያን አዲስ ዓመት ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ከተደመረው ኢሕአፓ) የተሰጠ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

አዲስ ዓመት በየጊዜው በወርሀ መስከረም ሲመጣ ሁልጊዜም ምድራችን በክረምት በነበረው ዝናብ ለምልማና ፍሬ አፍርታ እንዲሁም በአበቦች አጊጣ ስትታይ የሰው ልጅ በደስታና በተስፋ የሚሞላበት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ወቅት ይሆናል፡፡ በዚሁ መንፈስ የኢትዮጵ ያ ህዝብም የ2012 አዲስ ዓመትን በደስታና በተሰፋ ስሜት በዓሉን ያከብራል፣ ፈጣሪውንም ያመሰግናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) ለዚህ የደስታ እና የተስፋ በዓል የኢትዮጵያን ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ ! ይላል፡፡
ኢትዮጵያ በአለፈው የ2011 ዓ.ም. ከፍተኛ በሆነ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ በርካታ ህዝብ የተፈናቀለበት፣ የሞተበት እና ክፋትና ጥላቻ ያጠለለበት ዓመት ነበር፡፡ የሀገራችን ዋነኛ የፓለቲካ ችግር በአንድ ወገን ሀገራችንን በብሄር/በቋንቋ ለመበታተን የተነሱ ጽንፈኞች ከምንጊዜውም በላይ ስጋት መሆናቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገራዊ አንድነቱና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው፡፡
በ2011 ከአጋጠመን የሰላም ማጣት ብዙ ልንማር ይገባል፡፡ የሰላም ዋጋው ስንት ነው ብለን ጠይቀን፣ መልሱ መለኪያ የሌለው እጅግ ውድ መሆኑን መናገር ለቀጣዩ አዲስ ዓመት ለሰላም ለመታገል ያነሳሳናል፡፡ የሰላም ማጣት መነሻዎችና መፍትሄዎች ምንድናቸው ብለን ጠይቀን፣ አለመቻቻል፣ጥላቻ፣ ጭቆናና የህግ የበላይነት ያለመከበር ናቸው ብለን አነዚህን ምክንያቶች ነቅስን አውጥተን መታገል ይኖርብናል፡፡
ኢሕአፓ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ ሀገር ቤት ከገባ እነሆ 1 ዓመት ሊሞላው ነው፡፡ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የፓርቲውን መዋቅሮች

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.