ሊቨርፑል የጎል ናዳ ሲያዘንብ ሲቲ የመጀመሪያ ሽንፈትን አስተናገደ / የእረቡ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ውጤቶች

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/39873

አባይ ሚዲያ ስፖርት ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ፉክክር ለመግባት ሊቨርፑልና ስፓርታ ሞስኮ ያደረጉት ጨዋታ በጎል በተምበሸበሸ ምሽት ደምቆ ተጠናቅቋል።

ሊቨርፑል በስፓርታ ሞስኮ ላይ 7 ጎሎችን ባዘነበበት በዚህ ምሽት ፊሊፕ ኮንቲኖ 3 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ሃትሪክ መስራት ችሏል።

ከ 4ኛው ደቂቃ የጀመረው የሊቨርፑል የጎል ናዳ  እስከ 86 ኛው ደቂቃ ዘልቆ በጠቅላላው 7 ለ 0 በሆነ ውጤት ጣፋጭ ድልን ሲያጣጥሙ አምሽተዋል። 

ማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያውን ሽንፈት ከሻክታር ዶኔስክ ጋር ባደረገው ጨዋታ ቢያስተናግድም በምድቡ 1ኛ ሆኖ ሲያልፍ የዩክሬኑ ሻክታር ዶኔስክ በ2ኛ ደረጃ አልፏል።

ሪያል ማድሪድ ቦሪሲያ ዶርትመንድን 3 ለ 2 በማሸነፍ ማለፉን ሲያረጋግጥ በላሊጋው ኳስና መረብን እንደወትሮ ማገናኘት የተሳነው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ  በሻምፒየንስ ሊጉ ብዙ ጎል ያስቀጠረ ተጫዎች ለመሆን በቅቷል።

ቶትንሃም ተጋጣሚውን 3 ለ 0 በመርታት ከምድቡ በ 16 ነጥብ 1 ኛ በመሆን ቀጣዩን ዙር ሲቀላቀል ሪያል ማድሪድ በ2ኛ ደረጃ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብቷል። 

ቤሺክታሽ ላይፕሲግን 2 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቡ በ 1ኝነት ሲያጠናቅቅ ፖርቶ ሞናኮን 5 ለ 2 በማሸነፍ በ 2ኛ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

በዘንድሮው የሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ አምስት የእንግሊዝ ክለቦች (ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ፣ ቶትንሃምና ሊቨርፑል) ለማለፍ ችለዋል።

Share this post

Post Comment