ላሊበላን ለአደጋ በማጋለጥ ለመበልጸግ የቋመጡ የቅርስ ጥበቃ መስሪያቤት ሃላፊወችና ተባባሪወቻቸው በሕግ ሊጠየቁ ይገባል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/63778

(ሚኪ አምሃራ)
በላሊበላ ላይ ስለሚፈጸሙት ሁለት ሌብነቶችና መወሰድ ስላለበት እርምጃ በዚህ ዓጭር ገለጻ ላይ የቅርስ ጥበቃን ጥፋት በተመለከተ ስንናገር የቅርስ ጥበቃ ዓመራርን እና በተለይ ሃላፊውን እንጅ ሁሉም የቅርስ ጥበቃ ሰራተኞች ጥፋተኛ ናቸው እያልን ዓለመሆኑ በቅድሚያ ይታወቅልን።
ፍሬ ነገር:- ላሊበላን ለአደጋ በማጋለጥ ለመበልጸግ የቋመጡ የቅርስ ጥበቃ መስሪያቤት ሃላፊወችና ተባባሪወቻቸው ላሊበላ ላይ በፈጠሩት ዓደጋ በህግ መጠየቅ ሲኖርባቸው ዓሁንም ላሊበላን የማዳን ስራው መሪ መሆናቸው ዓስገራሚ ንቀት ነው። ላሊበላን ለማዳን የሚደረገውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ መደረግ ካለባቸው ሞያዊ ተግባራት በተጨማሪ በህንጻው ላይ ዓደጋ ያመጣውን ብልሹና ህሊና ቢስ የቅርስ ጥበቃ መዋቅር ስርዓት ማስያዝ መዋል ማደር የሌለበት ተግባር ነው። ይህ ተግባር ላሊበላን የማዳን ጩኸታችንን ያሰምርልናል እንጅ ዓይጎትተውም። ቅርስ ጥበቃ ላሊበላ ላይ ያሰራው ይህ መጠለያ ወንጀል ነው- እርዳታ ዓይደለም። ወንጀል የሰራ ደሞ በህግ ይጠየቃል እንጅ ወንጀል የሰራበት ቅርስ ጠባቂ ተደርጎ አይሾምም።” ይህ የህዝባችን እና ለህዝባችን የሚቆረቆሩ ባለሞያወች ድምጽ ነው። ህዝባችን “ለመሆኑ ባገሪቱ ውስጥ የተማረ የለም ወይ? በማን አለብኝነት እኛን እያስፈራሩ ህንጻውን ሊያፈርስ የሚችል ብረት ሲተክሉ ለምን ብሎ የሚጠይቅ እንዴት ይጥፋ? ካህናቱ ደብዳቤ ያልጻፍልነት የመንግስት ባለስልጣን ወይም ዓለማቀፍ ድርጅት የለም። ለምን ተናቅን? ቅርሳችንን ለሞት አሳልፎ የሰጠው አካል ይጠየቅልን” እያለ ነው።
ህዝባችን “ተጠያቂነት ከሌለ ዓሁንም ገንዘብ ዓሰባስበው መጥተው ህንጻችንን ሊያስፈርሱት ይችላሉ። ሁልጊዜም ቢሆን ገንዘቡ ላይ እንጅ ስራው ላይ ትኩረት ዓይሰጡም” እያለ ነው። ህዝባችንም በሰላማዊ ሰልፍ የቅርስ ጥበቃን ወንጀል ገልጻል። በባለሞያወች

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.