ላቲን የኦሮሞ ልጆችን ክፉኛ ጎድቷል #ግርማካሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139445


አባ አናሲሞስ ነሲብ፣ ከአንድ መቶ አመት በፊት መጽሀፍ ቅዱስን በኦሮምኛ በኢትዮጵያ/ግእዝ ፊደል የተረጎሙ የወለጋ አባት ነበሩ። የኦሮሞ አባት ያላልኩት አባ አናሲሞስ ኦሮምኛ ተናጋሪ የነበሩ ቢሆንም ኦሮሞ ስለመሆናቸው ግን ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነው። ለምን በወለጋ ብዙ ማህበረሰቦች ኦሮሞ ሳይሆኑ ኦሮምኛን ግን በግዳጅ እንዲናገሩ የተደረጉ ስላሉ።በወረራ። ( በነገራችን ላይ አጤ ሚኒሊክ ወለጋን በወረራ አላስገበሩም። ነገር ግን የኦሮሞ አባ ገዳዎች በወረራ ነው በዚያ የሚኖሩ ብሄረሰቦችን በነርሱ ስር ያደረጉት)
እንግዲህ ኦሮምኛ ቋንቋ በበቂ ሁኔታ በግእዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል ከአንድ መቶ አመት በፊት አባ አናሲሞስ አሳይተዉናል፡፡ በግእዝ ብቃት ላይ በርካታና ዝርዝር ሳይንሳዊ መረጃዎች በብዛት አሉ። ያለ ምንም ጥርጥር የግእዝ ፊደል ለኦሮምኛ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ ብቁ ነው። ብቁ ብቻ ሳይሆን ከላቲን በእጅጉ የተሻለ ነው።
ሆኖም የጥቁር ፈረንጆች የሆኑ፣ የኦሮሞን ማህበረሰብ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ለመነጠል የሚፈልጉ፣ ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር የሚጠየፉ ጠባቦች አሉ። ኦሮምኛ አባ አናሲሞስ እንዳደረጉት በግእዝ ፊደል ከተጻፈ፣ ኦሮሞ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ትስስሩ ይቀጥላል የሚል ፍርሃት ስላለባቸው፣ ለግእዝ ፊደል ካላቸው ጥላቻ የተነሳ፣ ሕዝብ ሳይፈልግ ነው ኦሮምኛ በላቲን እንዲጻፍ ያደረጉት። በግድ፣ በጉልበት።
ያንንም በማድረጋቸው በተወሰነ መልኩ ተሳክቶላቸዋል። ብዙ የኦሮሞ ልጆች ላቲን ብቻ ነው ማንበብና መጻፍ የሚችሉት። ግን የነዚህ ሰዎች መጠነኛ ስኬት ለኦሮሞ ማህበረሰብ ጉዳት ነው የሆነው። የግእዝ ፊደልን፣ አማርኛ እንዲጠሉ ተደርጎ ስላደጉ ፣ አማርኛ ማንበብን መጻፍ አይችሉም። ከዚህም የተነሳ ከተወሰኑ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች ውጭ ስራ የማግኘት እድላቸው ዜሮ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.