ሌብነት ላይ የተሰማሩ የትራፊክ ፖሊሶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘዴ ተጀመረ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79824

ሌብነት ላይ የተሰማሩ የትራፊክ ፖሊሶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድርግ መጀመሩን የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ።

የትራንስፖርት አገልግሎት ማህበረሰቡን በትክክል እና በተሣለጠ ሁኔታ ለማስተናገድ ያስችል ዘንድ የትራፊክ ፖሊሶች ሚና ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ የትራፊክ ፖሊሶች ከሙያ ስነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ አሽከርካሪዎች ህግና ደንብ በሚጥሱበት ጊዜ አጥፊውን ከመቅጣት ይልቅ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ሲቀበሉ ይስተዋላል።
ይህም አሽከርካሪዎችን ለተለያዩ አደጋዎች በማጋለጥ ለብዙ ሰዎች ህይዎት መቀጠፍና ለከፍተኛ ንብረት ውድመት የሚዳርግ መሆኑ መረጃዎች ያመላክታሉ ። ስለሆነም የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖረት ቢሮ የችግሩን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት የትራፊክ ፖሊሶችን ከዚህ መሰሉ ድርጊት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘዴዎች ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የባለስልጣኑ የትራፊክ ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ግርማ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ችግሩን በተመለከተ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፥ ችግሩን ለመለየትም የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
በዚህ መሰረትም በህግ ማዕቀፉ ላይ የተቀመጠውን ደንብ ድርጅቱ ወደ ቴክኖሎጂ በመቀየር አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ነው የተገለፀው።
ይህም ቅሬታ አቅራቢዎች ችግሩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የአጭር መልዕክት ፅሁፍ ቁጥር 85 84 ላይ ለባለስልጣኑ ጥቆማ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ነው ተብሏል ።
በሚቀርበው ጥቆማ መሰረትም በሌብነት ላይ የተሰማሩ የትራፊክ ፖሊሶችን በቀላሉ መለየት የሚያስችል መሆኑን አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል።
ተጠቃሚዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታ በተገቢው ሁኔታ ለማጠናከር ሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ መሰረትም ባለስልጣኑ በህገ ወጥ ድርጊት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የትራፊክ ፖሊሶችን ለህግ በማቅረብ ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.