ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ትግራይ ውስጥ የወርቅ ካባ እና አክሊል በመሸለማቸው ህወሓት ሸላሚዎቹን አገተ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75418

ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ትግራይ ውስጥ የወርቅ ካባ እና አክሊል በመሸለማቸው ህወሓት ሸላሚዎቹን እንዳገተና እንዳስፈራራቸው Amdom Gebreslasie ገልጿል፡፡ Wedi Shambel ፅሁፉን ወደ አማርኛ ትርጉሞታል፡፡
=====================================
“የህወሓት አፈና በሰበካ ጉባኤ ማርያም ንግድ”
የህወሓት ፅህፈት ቤት “ልኡል ራስ ስዩም መንገሻ እንደሚመጡ ለምን ቀድማችሁ ሪፖርት አላደረጋችሁልንም፣ ያለ እኛ ፍቃድ ወርቅ ካባ ሸልማችሃል” በማለት የካቴድራሉን የሰበካ ጉባኤ መሪዎች ደብረ ስብሀት ባእታ ማርያም (ማርያም ቡግሳ) 03/04/2011 ዓ/ም በተከበረበት ጊዜ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ነበሩ”

ልኡል መንገሻ የማርያም ቡግሳ የሰንበት ትምህርትን ያቋቋሙ በመሆናቸውና ለአደረጉት ብዙ አስተዋፅኦ ነበር የክብር እንግዳ የሆኑት ቤተክርስቲያንም ለአደረጉት ዘመን ተሻጋሪ መልካም ስራ የወርቅ ካባ እና አክሊል ተሸልመዋል”
ይሄ ሽልማት አክሱም ላይ ዶክተር ደብረፅዬን በአቡነ ማትያስ የተሸለመው የወርቅ ካባ በማወዳደር የህወሓት ፅህፈት ቤት ግን ስጋት አድሮባቸው ቁጣቸውን በመግለጽ አዘጋጅ ኮሚቴውን እና የሰበካ ጉባኤውን በማገት ትልቅ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሰጡዋቸው ይገልፃል”
በዛው ቀን
*ማርያም ቡግሳ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ማእርግ ተሰጥቷል
*በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ትምህርት ቤት አቋቁማ አስተምራ እንድታስመርቅ ይፈቅዳል
*ልኡል ራስ ስዩም መንገሻ በህዝቡ ፊት ወርቅ ካባና አክሊል ተሸልመዋል
*ህዝቡም ደግሞ በልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ስም በአስር ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፉን አድርጓል”

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.