ሕብር ራዲዮ – ፕሮፌሰር ዕዝቄል ጋቢና እና አቻመለህ ታምሩ ያደረጉት ውይይት ክፍል 2/2

Source: http://welkait.com/?p=11104

Share this post

One thought on “ሕብር ራዲዮ – ፕሮፌሰር ዕዝቄል ጋቢና እና አቻመለህ ታምሩ ያደረጉት ውይይት ክፍል 2/2

 1. ..የእስቄል ጋቢሳ ከፈረንጅ አፍ የወደቀ ጥሑፍ ገልብጦ ወይንም ውሸት ተራኪ በፈረንጅ ሥም የሚያሳትማት ወሬ ሁሉ ታሪክ ማድረግ ‘ማስረጃና መረጃን’ ለማቅረብ አዲስ ታሪክ እያዘጋጀን ነው ማለት አንዴ ያገደደ በሬ ለገደል ነው። ይልቅ አዳሜ የጎንዮሽ ስትፋተግ/ስትላፋ ትውልድ እያባላህ አታስበላ፡ የታገለ መስሎት እውቅና/ዝና ለማትረፍ ሚዲያ ላይና አዳራሽ ውስጥ ስትቦጠልቅ ብታድር ብትውል ድሃው አማራና ኦርሞ እንዲሁም አናሳ/የተረሱ ብሔር/ብሔረሰብ በቀጥታ የሚደርስባቸውን መገለልና የበይ ተመልካች መሆን ሀገርን በክልል ለውጦ ዜጋ እየተፈናቀለ እንደከብት በመኪና የሚታጨቅበት ጫካና ገደል ሥር የሚደበቅበት ሕጻናትና እናቶች ሀረጋውያን በሀገራቸው እንደ እርኩስ የሚባረሩበት የሚንገላቱና የሚራቡበት ዘመን እንዲያከትም አብሮ ሠርቶ አብሮ ማደግን መምከር በተሻለ ነበር።

  **በደህናው ዘመን እስቅኤል ጋቢሳ የሜንጫ አብዮትን ከመቀላቀሉ በፊት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጥናት ተንታኝ ነበር…በአንድ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፶ከመቶ ኦሮሞ ነው..፹፭ ከመቶ ኦሮሞ እስላም ነው…፷፭ ከመቶ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የኦሮሞ ነው፡ ፭፻ሺህ የሀገሪቱ ወታደር ኦሮሞ ነው።፸፭ ከመቶ የኢትዮጵያ ውሃ ከኦሮሞ መሬት ነው፡ ፻ ከመቶ የአዲስ አበባ ውሃና ምግብ የኦሮሞ ነው፡ የሚሉ የደደቢት የዋሻ ጨዋታ በሁሉም ክፍለ ክልሎችና የትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲዎች) ጸጋዬ አርአንሳ ያስተመረበት ሁሉ ከተበከለ በኋላ ዲያስፐር ውስጥ ተነዛ…ተንዛዛ…
  እስቃኤል ይህንን ሲሰማ “ቡና፡ ውሃ፡ ጥሬ እህል፡አሁን ላለንበት ዘመን መመኪያና መኩሪያ አይሆንም፡ ዘመንና አየር ንብረት ሲለወጥ ብዙ ፈተና አለ፡ ለምሳሌም _፟ በቻይና ከ፮ሺህ በላይ የውሃ ምንጮች መድረቃቸው ተዘገቧል”ብሎ ነበር ያ የሚያሳየው ድሮ ለመገንጠልና ሌላውን ለመግደል የሚደረግ ቱልቱላ ጉንጭ አልፋ ቡልጠቃ የአዕምሮ እጠበት(ማለቅ(ቃ)ለቅ) እንደሆነ ነው።
  ** ይህ ሀሳቡ ከነጭ ይልቅ ያልተነገራላቸው፡ ያልተደመጡ፡ ያልተፎከረላቸው ገበሬዎች ይስማማል ። ከዶ/ር ለማ መገርሳ የፖለቲካ ተኮር ንግግር(አዲስ አበባ የኦሮሞ ማዕከል..ባሕር ዳር የኦሮሞ ማዕከል የውጭ ዜጋና መንግስት ይመስል የመሬት ካርታ ከማሳድደ!? ይልቁንም ክልልን አስፍቶ የእውቀትና የሙያ ልዩ ግንኙነት ‘ኦሮሞው አማራ ውስጥ አማራው ኦሮሞ ውስጥ በሙያውና ችሎታው እንዲሰራ ድልድይ ይገነባል ብዬ ጠብቄው ነበር!!
  ** በእጥፍ ሊጨበጨብላቸው የሚገባ፡ የተረሱ የኦሮሞ ገበሬዎች፡ ከአባይ ወንዝ እሰከ ባሕር ዳር ያዩትን ምን አሉ
  “ጎጃም ይህ ሁሉ መሬት ላይ ጤፍ ዘርቶ፡ የከብቱ ብዛት፡ ወተቱ/ቅቤው ማሩ ለም ሀገር ነው ጉድ አየን!.. ይህ ሁሉ ሲሰበሰብ ለጎጃም ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ሁሉ ይበቃል… እናንተ ይህ ካላችሁ ኦሮሞ በቆሎ መኬ ጥራጥሬና ቡና ካለው ችግር የለብንም አሉ..” ግን ይህ ሁሉ ተመርቶ የአማራና ኦሮሞ ገበሬ እየተራበ ማን በላን!?”
  ይህ የሚያስተምረው’ተከልክለውና ተከልለው’ ካርታና ቋንቋ እያሉ በደረቅ መሬት ደረቅ ተስፋ የመጃጃል ቁጭት ነው!
  » ዛሬ አለን ተብሎ የሚያስፎክር ነገር የለም ጫት እንኳ ስንቱን በመንጫ እንዳናጨ ማየት ነው።
  _ በተመሳሳይ ኩቤክ ካናዳ ‘የሬድ እንዲያንስን’መሬት ከንግሊዝ ጦረኞች ተሻምታ፡ ከፈረንሳይ ሀገር መንገድ አዳሪና የሰው ነፍስ አጥፊ ቀማኛ እስረኞችን ጠራርጋ ወስዳ አስፍራ ዛሬ ባለ ሀገር ነን ብለው እገነጠላለሁ ትላለች!? *ሞኝ የኦሮሞ ኤሊት(ኤሊ) ይህንኑ ሲቀባጥሩ ይህንን ገልብጥው ሕዝብ ያጃጅላሉ። ኩቤክ(ፈረንሳይ)እንግሊዝም እሰው ሀገር መጡ እንጂ የክፍለ ሀገር ነባር አደሉም። ለመሆኑ ቋንቋን በጋራ እየተጠቀሙ ለምን መገንጠል ፈለጉ? ኩቤክ ለኒው ዮርክ ቅርብ ስለሆነች ያላትን መብራት ሁሉ በዶላር በመሸጥ ሕዝቤን አስተዳደራለሁ አለች…ባለፉት ፴ ዓመት ውስጥ ኒው ዮርክ ከንፋስና ከጸሐይ ተጠቃሚ ሆና፡ * የውሃ ኅይል መብራት ገበያው ፶ ከመቶ ቀነሰ!.. ጭራሽም ኒውዮርክ በበጋ በርካሽ ገዝታው በክረምት ኩቤክ(-፬፭)ዲግሪ ሴ..ስትበረድ ዶላሩን ከካናዳ ዶላር በክረምት አስወድደው መልሰው ለራሷ ለኩቤክና አጎራባች የካናዳ ሀገር ከተሞች ኅይል መሸጥ ጀመሩ።በበጋ ደግሞ የዶላሩን ዋጋ ጥለው ቱሪስት(ጎብኚ) ሆነው ይፈንጩባቸዋል፡ ግሎባላይዜሽን! አሜሪካ በነጻ አበራ ይልሃል ይህ ነው። ብትገነጠል ንብረቷን ይዛ ኒውዮርከር ለመሆን የቋመጠችው ኩቤክ በአንድ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ሙከራ አጅሬ እንግሊዝ ትላልቅ የንግድ መርከብ ያላቸውን ጫኝና አወራጅ ጣሊያን፡ ግሪክ፡ ጀርመንና ቫልካን ሀገሮችንን አስበርግጎ ወደ እንግሊዘኛው ተናጋሪ ወደብ በቅናሽ እንዲያዛወሩ አደረጋቸው ሱቆቻቸውንም ዘጉ ሞት ሁለት በሉ።አሁን የኩቤከ ሕዝብ ከአውሮፓ ለመጣ ዕቃ ከእንግሊዝ ወደብ ቀረጥና ትራንስፖርት ከፈሎ ሕዝቡን ይቀልባል።
  “ልታስነቀስ ሄዳ አስነቀላ መጣቸ ማለት ይህ አደለምን!?
  ___ ኩቤክ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዢ ሀገሮችን ስታስገባ እንግሊዝ የራሱን ባሮች ቅድሚያ እየሰጠ ትልቋን ከተማዋን ሞንትሪያልን ፶ ከመቶ የእንግሊዝ መፈንጫ አደረገው።አሜሪካ ብቻ ባላት የንግድ (ኢንቨስተመንት)፸ሺህ ዜጎቿን ታኖራለች። ግማሹ ተዋልዶ ተጋብቶ ግማሹን መሬት ይዟል፡ ኩቤከርስ እንግሊዘኛ ስለማይችሉ ለአሜሪካ ኢንቨስተመንት ሁሉ ስደተኛው አራትና ከዚያም በላይ ቋንቋ በመቻሉ ሕገመንግስታዊ’ልዩ ጥቀማጥቀመኛ ሆነ’ ኩቤከርስ እንግሊዘኛ ለመማር ተገደዱ’። አስገንጣይ የፖለቲከኛ አተራማሽ ልጆቻችው ግን አሜሪካና እንግሊዝ የግል ትምህርት ቤት ወስጥ ናቸው እነሱም ቢያንስ ሶስት ቋንቋ ይችላሉ አብዛኛውም ከሁለት ዘር የተወለዱ ከሌላም የተጋቡና የተዋለዱ ናቸው(ፈረንሳይ አባቱን አያቅም ያለው ማን ነበር?)።
  **በመጨረሻም ጓዶች ውይይታችሁ ባልከፋ ለወደፊቱ ይህ ሁለት ትልቅ ሕዝብ ከምትሉና ከምታሽሟጥጡት ትናንት ‘ደምህ ደሜ’ ብሎ በማግስቱ አንገቱ እየተቀላ ገደል የሚጣል ሕዝብ ከአማራና ኦሮሞውም ውጭ የተረሳና አናሳ (ብሔር፫ ብሔረሰብ፪ ሕዝቦች፫) የተባሉትም ትግራይና ኤርትራውያንንም ጨምሮ እራሳቸው እየገቡ ይናገሩ ይመስክሩ ነፍጠኛ ወራሪ ማን እንደነበር ያስረዱን የበለጠ ከቃልም በላይ ማስረጃና መረጃ ይኖራቸዋልም። የሁለት ወገን እሰጥ አገባ ብቻ ሀገር አያቆምም!።፡ሚዲያና ቦታ የላቸውም ብላችሁ አትርሷቸው አደራ! በአንድ ወቅት የኢሳት ጋዜጠኛ የደቡብ ሰው ጠየቀ “በድሮ ዘመን አትዘፍኑም ባሕልና ቋንቋችሁ፡ አይፈቀድም፡ እንዲያውም በምንይልክ ዘመን ድምጻችሁ ማይክራፎን ይሰብራል ተብሎ ትከለከሉ ነበር” አላቸው ግልሰቡም በፈገግታ ሲመልሱ “ቋንቋው ስለነበር አሁንም እንጠቀምበታለን፡ አሁን ፈጥሮ የሰጠን የለም። ዘፈንና ጭፈራችንም አሁን የተማርነው አደለም ከጥንት ከቤተሰቦቻችን የነበረ የወረስነው የሚቀጠል ነው። ለዘፈን ማይክ የመከልከሉ ጉዳይ ምንይልክ ስንት ማይክራፎን ቢኖራቸው ነው? አሁን ብዙ ሚዲያና ማይክራፎን አለ አሁን ነው በአንደበታችን መናገር የተነፈግነው ብለው ጋዜጠኛውን አስቆሙት።”

  **ሠላም ለሁሉም አንድነት፡ ኅብረት፡ከፖለቲካው ይልቅ ለዚህ ደሃ፡ የዋህ፡ ጨዋ ሕዝብ የክክል እስረኛ ሳይሆን የዕውቀት፡ የኢኮኖሚ፡ ቲክኖሎጂና ፍትሃዊ የአንድ ሀገር ዜጋ ሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆን ጠንክረን እንሥራ።በለው!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.