ሕወሃት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም ተባለ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%88%95%E1%8B%88%E1%88%83%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B8%E1%8A%B3%E1%8B%AD-%E1%8C%8A%E1%8B%9C-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%AB-%E1%88%88%E1%88%9B%E1%8A%AB%E1%88%84%E1%8B%B5-%E1%8B%A8/

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010)

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሕገ መንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ እንደማይቀር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ።

ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት ኢሕአዴግ እንደ ፓርቲ የመቀጠልና ሀገር የማስተዳደር ሕልሙ በማክተም ላይ ነው።

የኢትዮጵያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ወቅታዊውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

እናም ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት ሕዝብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ባለመስጠቱ ሀገሪቱ አደጋ ላይ ወድቃለች ።

ገዥው ፓርቲም ባሉበት ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተነሳ ሀገር ማስተዳደር አቅቶታል ነው ያሉት።

ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ ቢልም ያለውን በተግባር መተርጎም እንዳቃተውም ዶክተር ነጋሶ ገልጸዋል።

የሕዝብ ጥያቄዎችን በአግባቡ አለመመለሳቸውም አሁን በሀገሪቱ ያለውን ችግር ለማባባስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

እንደ ዶክተር ነጋሶ ገለጻ የሕዝብን ጥያቄ መፍታት ባለመቻሉም ኢሕአዴግ በሕገመንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል።

እርሳቸው እንደሚሉት ኢሕአዴግ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ያለውን ችግር ብቻውን ሊፈታው አይችልም።

እናም በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመምከር ምላሽ መስጠጥ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ይላሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን ማድረግ ካልቻለ ኢሕአዴግ እንደ አንድ ፓርቲ የመቀጠልና ሀገር የማስተዳደር ሕልሙ ጨርሶ ያከትማል።

Share this post

One thought on “ሕወሃት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም ተባለ

 1. >»ቱልቱላ፡ ጡሩንባ ለመሆኑ ኢሳትና ነጋሶ ጊዳዳ ሕገመንግስት እንዴት ገባቸው!?
  * ነጋሶ እንኳን ከጀርመን በኦሮሞ ምሁርነቱ ተፈልጎ በሻቢያ ህወሓት ኦነግ ጋብቻ ላይ በመፈረሙ አዋቂ ካደረገውና አንድ ቀን አልገባኝም፡ሌላ ግዜ ሕዝብ አልተወያየበትም፡ ሌላ ግዜ በችኮላ ያፀደቅነው እንጂ እንወያይበታለን ብለን ያለፍነው ነው” እያለ ነጋሶ ፕሬዘዳንትነትና አዲስ አበባ ከንቲባን በሞኖፖሊ መያዙ ልዩ ተጠቃሚ አድርጎ እንደከብት ሲነዳ መኖሩን ዘነጋው ልበል?

  *በቃለመጠይቁ ሁሉ ይቀባዥራል ይቀባጥራል…እንዲሁ ሀገር፡ፓርቲ፡ መኖሪያ ቤት፡ፓርቲና ሐሳብ ሲቀያይይር በመንገድ መሞቱ ነው።
  *አዳሜ የሻቢያህወሓት መጋዣ ሆኖ የኦሮሞ ልጅ ሲመክንና ሲባክን የበይ ተመልካች ሲሆን አማራና ኦርቶዶክስ እስኪጠፋ ደህና ነበሩ..”ዘመኑ የኢትዮጵያ ከፍታ ነው!” ሲባል እያንዳንዱና ሁሉ አድርባይ! አውርቶ አደር! ልዩ ጥቅማጥቅመኛ ለቀቁ፡ጠፉ፡ተሰናበቱ፡ተጣሉ፡ተገነጠሉ፡በተሰባበረ የእሳት ወሬ ታጭበረብራላችሁ፡ ይኸው ታማኝ አገልጋያቸው ከፓርላማ ወጡ ሲባል “አለሁ አሉ” ለምን? ከተማ እንዳይስፋፋ ያሳደሙ፡ ሀገርና ንብረት እንዲያወደሙ ያሸበሩት ሜ/ጀ አባ ሚናሴ ተ/ኖት የጀዋሪያንን የዲያስፐር አጀንዳ አስፈጽመው ለቀቅሁ አሉ፡ እንግዲያው በአንተ ቃል ከአዲስ አበባ መስፋፋት ተቃውሞ ጀምሮ አሁንም ሕዝቤና ፓርቲዬ ተበሳቁሏል ተንቋል ብለህ ወጣት አልቋልና ትጠረነፋለህ ሲሉት ፓርላማውን ስጡኝ አለ።
  ” እንደ ዶክተር ነጋሶ ገለጻ የሕዝብን ጥያቄ መፍታት ባለመቻሉም ኢሕአዴግ በሕገመንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል።” ድንቄም “በሕገመንግስቱ አስቸኳይ ምርጫ” ማን ሰው አለሽና መንገድ ላይ ታፏጫለሽ አለ… አይሆንም እጂ ይህንን ካደረጉት ኦሕዴድ በክልሉ እንዲሸነፍ አድርገው ኦፌኮን አስመረጠው ሁላችሁንም ከጫወታ ውጭ እንደሚያደርጉና ሁሉንም ከሰው ወፌ ላላ እንደሚወርድ እወቁ። ..አለዚያ አብዮታዊ ግንባርን አፍርሶ፡ አንድ ወጥ ፓርቲ አድርጎ፡ ኦህዴድና ኦፌኮ መድረክን አፍርሶ፡ አጋር ፓቲና አዲስ ተፈልፋይ ልዩ ተጠቃሚዎችን በፓርቲ አደራጅቶ ሁሉንም የድሮ ሥራዓት ተጠቃሚ/ተድጋፊ ቢሮና ጎራ አፍርሶ ይበትናችኋል።እዚያም ቤት እሳት አለ ታዘበኝ! እነሱ አድራሻና አዳራሽ ዘግተው በሕዝብ ሲጫወቱ አዳሜ ህወሓት በወሬ በአዳራሽ ጭብጫባ፡ በሚዲያ መፈክር፡በመግለጫና የቡድን ሰነድ ይወድቃል በልና አፍከን ከፈተህ ጠብቅ።
  ኢሳት የፖለቲካ ላጲሶችን በጣም ይወዳል… እውነትም ጃዋር ያስተማራቸው የቦለጠቀላቸው አልገባቸውም!? ዋ

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.