ሕወሓት የሚያወጣቸው መግለጫዎች የተሳሳቱና በሕዝብ ውስጥ መደናገር እየፈጠሩ ናቸው – ኢሕአዴግ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/158712

ሪፓርተር

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የግንባሩ አባል የሆነው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሰሞኑን የሚያወጣቸው መግለጫዎች፣ የተሳሳቱና በሕዝብ ውስጥ መደናገር እየፈጠሩ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡
ከኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ማምሻው ላይ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በሕወሓት የኢሕአዴግን ውህደት አስመልክቶ የሚሰጡ መግለጫዎች የተሳሳቱና አደናጋሪ በመሆናቸው ለሕዝቡ ጠቅለል ያለ መረጃ መስጠት አስፈልጓል፡፡
ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ኅብረ ብሔራዊ ውህድ ፓርቲ ለማሸጋገር በ1996 ዓ.ም. ከተካሄደው አምስተኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ መቆየቱን የሚገልጸው የኢሕአዴግ ምክር ቤት፣ በተለይ ባለፈው ዓመት በሐዋሳ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የጥናት ሥራው በቶሎ ተጠናቆ የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ውህድ ፈጥረው ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር መወሰኑን ገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የውህደቱ አቀንቃኝ ሆኖ ውህደቱን ሲመራ የነበረው ሕወሓት ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውህደቱ ላይ አሉታዊ ገጽታ ያላቸውን ተደጋጋሚ መግለጫዎች እያወጣ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ‹‹ሕወሓት እንደ ድርጅትም ሆነ በአንዳንድ አመራሮቹ በተደጋጋሚ የሚሰጣቸው መግለጫዎች በሁለት መሠረታዊ  ምክንያቶች ስህተት ሆነው እናገኛቸዋለን፤›› ያለው የኢሕአዴግ ምክር ቤት፣ የመጀመርያው ስህተት ከድርጅት አሠራርና ዲሲፕሊን ጋር ሲያያዝ ሁለተኛው ስህተት ደግሞ ይዘቱ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ሕወሓትን ጨምሮ ሌሎች አጋርና አባል ድርጅቶች ኢሕአዴግን ወደ ውህደት የሚያሸጋግረው ጥናት በአፋጣኝ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ያለ ልዩነት መወሰኑን መግለጫው አስታውሶ፣ ሁሉም ድርጅቶች በጥናቱ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተው ጥናቱ እንዲዳብር

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.