“ሕዝብን ከማገልገል በላይ ክብር የለም”- አዲሱ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ – BBC News አማርኛ

“ሕዝብን ከማገልገል በላይ ክብር የለም”- አዲሱ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/1491E/production/_114945248_121622067_1383442708497386_9005132986349793957_n.jpg

በትናንትናው ዕለት፣ ጥቅምት 6፣ 2013 ዓ.ም ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በስራ አመራርና ፍልስፍና ቻይና አገር ከሚገኘው ኋጁንግ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ አጠናቀው የመጡት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የምሁራን ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪ፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የከተማ አደረጃት አማካሪና በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ካገለገሉባቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባነታቸው ሊያከናውኗቸው ያሰቧቸውን እቅዶችና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply