መልስ ለአምሳሉ ገብረኪዳን ጽሑፍ ከአንዱዓለም ተፈራ፣ ከተጠቀሱት ድርጅቶች ወስጥ የአንደኛው አባል

Source: http://www.aapo2nd.org/?p=1380

የ “ቤተ አማራ” ወይም “ዳግማዊ መአሕድ” ነን ባዮች ማንነትና ስውር የጥፋት ዓላማ ሲጋለጥ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሳተናው ድረገጽ ላይ May 10, 2017 23:40 የወጣ
መልስ ከአንዱዓለም ተፈራ ከተጠቀሱት ድርጅቶች ወስጥ የአንደኛው አባል

አንድ ወንድሜ ይሄ ጽሑፍ መውጣቱንና ጊዜ ካለኝ እንዳነበው መከረኝ። አልፈለግሁም ነበር። ነገር ግን፤ ወንድሜን በጣም ስለማከብረውና እሱን ይሄን ያህል ካሳሰበው፤ መልዕክቱን መረዳት አለብኝ ብዬ፤ ላነበው ጎራ አልኩ። ዐቅል ኖሮኝ አንብቤ ስጨርስ፤ የተለያዩ ሃሳቦች በአእምሮዬ ተተራመሱ። ባንድ በኩል፤ የጸሐፊውን የአእምሮ ዕርጋታ ለመገምገም በሚያስችል ሁኔታ ስላስቀመጡት፤ ለዚህ ምንም ዓይነት መልስ መሥጠት ተገቢ አይደለም አልኩ። ትክክልም ነው። መልስ አለመሥጠት፤ ራሱን የቻለ መልስ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ጸሐፊው መልዕክቱን ልከዋል። ከፋም በጄም የልባቸውን አድርሰዋል፤ እፎይ ብለው ተኝተዋል። ይህ በሌሎች ምን ይፈጥራል? የሚለውን ስጤን፤ መቼም የተጣለ መርዝ መውደቂያ ካገኘ ጉዳት ማድረሱ አይቀርምና፤ ትክክለኛውን በቅጡ ማስቀመጡ ተገቢ ነው፤ አልኩ። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፤ እንዲህ በዐማራዎች መካከል ዐማራ ሆኖ፤ ከሥር መሠረቱ ለመረዳትና ሁኔታውን ለማወቅ ጥረት ከማድረግ ይልቅ፤ ዝልፊያና ፉከራ የገቡ ሰውዬ፤ አሁንም ወደድንም ጠላንም ዐማራዎችን ነው የሚያስገምተን። እናም የለም፤ ትክክለኛው እንዲህ ነው! ማለቱን አስፈላጊ ሆኖ አገኘሁት። የለም የምለው ግን ለጸሐፊው አይደለም። ጸሐፊውን አስተካክላለሁ የሚል እምነትም ፍላጎትም የለኝም። በግርግጥ ከእንቅልፋቸው ቢነቁ ደስ ይለኛል። አውቀው ከተኙበት ግን በግድ ቀስቅሼ እንደማይሳካልኝ ስለማውቅ፤ አልሞክረውም። ነገር ግን፤ ጽሑፉ ለደረሳቸው፤ በተለይም የኒህን የዐማራ ወጣቶችን እንቅስቃሴ የሚከታተሉትን ዐማራዎች፤ ምንም በዚህ ጽሑፍ ወዲያ ወዲህ ይላሉ የሚል እምነት ባይኖረኝም፤ እግረ መንገዱን የወጣቶቹን ልፋት ግልጽ ያደርጋል በማለት፤ መልስ ለአምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው በሚል እንደሚከተለው አስቀመጥኩ። አንድ በአንድ የጽሑፉን ዓረፍተ ነገሮች እየተነተንኩ ፍሬ ሃሳባቸውን ከጥንካሬና ደካማ ገፅታቸው ጋር ላስቀምጥ ብል፤ ደጎስ ያለ መጽሐፍ መድረስ ሊኖርብኝ ነው። ዐቅሉ ኖሮት የሚያነበው ስለማይኖር ተውኩት። ይረዳችሁ ዘንድ ግን፤ በጽሑፉ የቀረቡትን ወንጀሎች በማስፈር፤ ትክክለኛነታቸውን ወይንም ትክክለኛ አለመሆናቸውን ማቅረቡ የተሻለ ሆኖ አገኘሁት። ወንጀሎቹን ልዘርዝር፤ ፩ኛ. “ . . . እጅግ በሚያሳዝን መልኩ እስከ ትናንትና ድረስ ስከታተላቸው ሊያደርጉት አልቻሉም አልፈቀዱምም፡፡ ሰዎቹ በዚያ ጽሑፌ ላይ ሁሉም የአማራ ድርጅት በጉባኤው እንዳይገኙ የሚከለክላቸው ምንም ዓይነት ምክንያት ወይም መሰናክል እንዳይኖር ትሁትና አስተዋይ በሆነ አቀራረብ እየቀረቡ ሁሉንም እንዲታደሙ እንዲያደርጓቸው የጣልኩባቸውን አደራ አደራውን የመወጣት ብቃት ፍላጎትና ዓላማ ፈጽሞ የሌላቸው ተመሳስለው ገብተው ብቻ ሕዝቡን የመጥለፍ ስውር ዓላማ ያነገቡ በመሆናቸው . . . ” ይህ የመጀመሪያው ወንጀል ነው። ጸሐፊው፤ ባለፈው ጊዜ የጻፉትን አስመለክቶ፤ “አቤት ጌታዬ! እሽ! እርስዎ እንዳሉን እናደርጋለን!” ብሎ እጅ ነስቶ፤ ላደረጉት ጥረት፤ ሽልማት የሚሠጣቸው አካል ይጠብቁ ነበር። ይህ አለመደረጉ ወንጀል ነው? ወይንስ አይደለም? የሚለውን ለናንተ እተወዋለሁ። እኔ ያን ጽሑፋቸውን ጥሩ ጻፉ ብዬ፤ አድንቄያቸው ነበር። አሁንም ያ ጽሑፋቸው ድንቅ ነው። ይሄኛው ግን ገርሞኛል። እኔ መቸም ስድብ አላደገብኝም።………. read in pdf መልስ ለአምሳሉ ገብረኪዳን ጽሑፍ

Share this post

One thought on “መልስ ለአምሳሉ ገብረኪዳን ጽሑፍ ከአንዱዓለም ተፈራ፣ ከተጠቀሱት ድርጅቶች ወስጥ የአንደኛው አባል

 1. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)
  I like to apologize my readers for not using our Geez language. This is because, I clicked the “G” button to use the Geez button, unfortunately, the command key was not friendly and decided to use English to respond to my friend Ato Andualem Tefera for his critique against Seali Amsalu G/kidan.
  Let me copy and paste what Amsalu said on his his critique “የ “ቤተ አማራ” ወይም “ዳግማዊ መአሕድ” ነን ባዮች ማንነትና ስውር የጥፋት ዓላማ ሲጋለጥ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ሳተናው ድረገጽ ላይ May 10, 2017 23:40
  regarding Amsalu’s critique Andualem responded “መልስ ለአምሳሉ ገብረኪዳን ጽሑፍ ከአንዱዓለም ተፈራ፣ ከተጠቀሱት ድርጅቶች ወስጥ የአንደኛው አባል.
  (1)
  Andualem Amsalu wrote
  (“ምን ታረጉታላቹህ የእርግማን ልጆች በመሆናቸው እኮነው እንዲህ ዓይነት ጉድ ፍጥረቶች ለመሆን የተገደዱት።” )

  Andualem responded to the above phrase/sentence as the following

  ( “ብለውን እርፍ! የዚህኛው የጉድ ነው። ዘጠነኛውን ወንጀል ማለቴ ነው።” ብለው ብለው የአባትና የናት መረገምን አመጡት። እውነትም ጸሐፊው፤ የኒህ ወጣቶች ወላጆች ሲረገሙ በቦታው ከነበሩ ስህተቱ ከኔ ነው። የተረገሙ አባትና እናት ያላቸው ሰምቼም ዓይቼም ስለማላውቅ ነው። እኒህ ጸሐፊ ተዓምረኛ ናቸው! የተረገሙና ያልተረገሙ ወላጆችን ይለያሉ። እኔ ደግሞ እሳቸው በዐማራነታቸው ካልተረገሙ ወላጆች ስለመጡ፤ እንደኔው ያልተረገሙ ወላጆችን ብቻ የሚያውቁ አድርጌ ወስጃቸው ነበር። እሳቸው ግን የተረገሙትንም ያውቃሉ። እየጠየቅሁ አይደለም፤ እንዴት የተረገሙ ወላጆች እንደሚታወቁ መማሩን አልፈልግም! )

  Though, I am not Amharic speaker as brother Andualem, I think there is misunderstanding in part with Andualem Tefera with his interpretation. If I did misunderstand him, my apology and let me be corrected. When one used the term “የእርግማን ልጆች” is the opposite of “Yetebareku Lijoch”. In this case “የእርግማን ልጆች” does not necessarily pin point the cursed party are the parents. It means the mentioned elements/ parties/ are the outcome of a curse. It is not the parents who are cursed and born a cursed kids (though many people directly understood it as such) the right interpretation of the message is to pin point that either the parents or some other parties or God cursed them and came out as “cursed elements” (they are the result of a curse). The parents are not the curse, but the kids came out as curse due to a result of a cursed command. As we can similarly say “Ytebareku LiJoch” (kids of blessed), one also comes out as a result of curse. The curse can be from the mouth of the parents or God or any other parties or elders. Look at these two opposite terms both does not show necessarily pin point to parents “የእርግማን ልጆች” is the opposite of “Yetebareku Lijoch”.
  ———————————————–
  (2)- I am really confused when it comes to Bete Amhara organization. I do not know how many Bete Amhara there are, but, the one posted variety interviews on You Tube with Bete Amhara personalities Lidia Zewdu and Mesafint Bezaw claimed they are leaders/founders of the organization and claimed they for establishing Amhara country apart from Ethiopia. In fact the young lady Lidia in fact sounds as OLF/TPLF calling Ethiopia as combination ofd different Union (different country- not to mention the less values she gave to Ethiopianism. She is just premature ludicrous and defeated young lady)…. Therefore, I don’t know if both gentlemen are talking about this Bete-Amhara or any other Bete-Amhara if there is one with the same name; but if Andualem seemed to not heard this organization what they are struggling for——– I do not know. If Andualem is talking about another BeteAmhara (if there is another- which I do not know—-) or this I mentioned above, then Amsalu is right. They promulgated openly on media for cession.
  ———-By the way, there are some elements even in Dagamawi MAD that I have recorded their filthy racist mouth commenting one ethnic population as a whole. So, we got a lot of miles to walk. Anyways, I am glad Andualem is a member of those mentioned organization. I said this because, he had a reservation about them which he explained to me some times in the past for one of the reasons that Amsalu is accusing some elements of these organizations.

  Any ways, it is good to see revising ideas and reorganizing again as Andualem did with these elements. Similarly as Amsalu asked/ emailed me to apologize to G7/ESAT one time in the past but, glad I saw him at the end lined up his position with me. So, it is good to revise positions for good.
  Thanks
  GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

  Reply

Post Comment