መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ተቋማትና ግለሰቦች በሕግ እንደሚጠየቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ተቋማትና ግለሰቦች በሕግ እንደሚጠየቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎችን በመለየት ስራ መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች በሕግ እንደሚጠየቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጧል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት አባተ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የመንግሥት ይዞታ የሆነን መሬት በማደራጀት የሕዝብንና የአገርን ፍላጎት መሰረት አድርጎ የሚያለማ ነው። ለዓመታት ታጥረው አገልግሎት የማይሰጡ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች በአገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል ብለዋል። የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫኔ ሽመካ በበኩላቸው የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የመሬት ይዞታዎችን ለመለየትና ለማደራጀት የሚሄድባቸው ተቋማት መተባበር አለባቸው ብለዋል። መረጃ የሚጠየቁ የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች የተቋሙን ዓላማ በአግባቡ ተረድተው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡም አሳስበዋል። ከዚህ ባሻገር ኮርፖሬሽኑ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች ለመስጠት የማይተባበሩ ግለሰቦችና የመንግሥት ተቋማት አዋጁን እንዳልተቀበሉ ይቆጠራል ነው ያሉት። የአገሪቱ ከፍተኛው የሕግ አውጪ አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀውን አዋጅ ገቢራዊ አለማድረግ ሕግ መጣስ በመሆኑ መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ሁሉ ተጠያቂ ይሆናሉም ብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply