መራጮችን ወደሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት እንዲቀይሩ በማድረግ የምርጫ ሂደቱን ያስተጓጎለ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/171517

(አቶ) ተስፋዬ ዳንጊሶ የተባሉ ግለሰብ የምርጫ ጣቢያ ውስጥ ሰልፍ የማስተባበር ስራ በመስራት ሽፋን መራጮችን ወደ ሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት በማየት፣ ምልክቱን እንዲቀይሩ በመንገር ከዚያም ስማቸው ተጣርቶ አቤቱታ ሲቀርብ ስማቸውን በመደበቅ የምርጫ ሂደቱን ሲያስተጓሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና ማጣራት እንዲደረግባቸው ማድረጉን ለመግለጽ ይወዳል፡፡”
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰልፍ በማስተባበር ሽፋን፣ መራጮችን ወደሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት እንዲቀይሩ በማድረግ የምርጫ ሂደቱን ያስተጓጎለ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
እንደሚታወቀው የምርጫ አፈጻጸም ሂደቶችን በእውነተኝነት እና በገለልተኝነት የመተግበርና የመከታተል ሃላፊነት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት እንዲሁም በምርጫ አዋጁ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ሃላፊነት ነው፡፡

ማንኛውም ሌላ ግለሰብ የምርጫ/ የህዝበ ውሳኔ አፈጻጸምን ለመቀየር ለማወክ ወይም ሌላ መሰል ተግባራትን ለመፈጸም የሞከረ እንደሆነ በህግ እንደሚጠየቅ የተሻሻለው ኢፌዴሪ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 466 እስከ 476 በተመለከተው ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት ቦርዱ ከህዝብ በደረሰ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቆማ እንደደረሰው እንዲሁም የቦርዱ ሰራተኞች እንዳጣሩት መሰረት ተስፋዬ ዳንጊሶ የተባሉ ግለሰብ፣ የምርጫ ጣቢያው ውስጥ ሰልፍ የማስተባበር ስራ በመስራት ሽፋን፣ መራጮችን ወደሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት በማየት፣ ምልክቱን እንዲቀይሩ በመንገር ከዚያም ስማቸው ተጣርቶ አቤቱታ ሲቀርብ ስማቸውን በመደበቅ የምርጫ ሂደቱን ሲያስተጓጉሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌደራል ፓሊስ በቁጥጥር ስር እነዲውሉ እና ማጣራት እንዲደረግባቸው ማድረጉን ለመግለጽ ይወዳል፡፡
(የኢትዮጵያ ብሔራዊ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.