መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት መታሰቢያ ዕለት ሆኖ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ዘምዕራብ አርሲ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      መስከረ…

መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት መታሰቢያ ዕለት ሆኖ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ዘምዕራብ አርሲ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረ…

መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት መታሰቢያ ዕለት ሆኖ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ዘምዕራብ አርሲ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፤ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም የ21 ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት መታሰቢያ እንዲሆን የታወጀ መሆኑን አስታውቀዋል። በዕለቱም በሀገረ ስብከታቸው በሚገኙ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መርኃ ግብራት እና በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ እንዲውል መመሪያ አስተላልፈዋል። የመታሰቢያ መርኃግብሩም መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገረ ስብከት ደረጃ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተለየ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንደሚታሰብ በብፁዕነታቸው የተፈረመው ደብዳቤ አመልክቷል። መርኃ ግብሩ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ 111 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚከናወን መሆኑ ልዩ የሚያደርገው ሲሆን በሻሸመኔ ከተማ 10 የከተማውን አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናንን ያሳተፈ እንደሚሆን ይጠበቃል። መርኃ ግብሩ በተለይ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ሀይማኖት ተኮር ጥቃት መፈፀሙ፣ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፣የምዕመናን ሀብት ንብረት መዘረፉና መቃጠሉ፣ ከምንም በላይ ደግሞ በርካታ ኦርቶዶክሳዊያን ሰማዕትነትን መቀበላቸውን የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በመሆኑም በ21ኛው ክ/ዘመን የተገኙና በሀይማኖታቸው ምክንያት ሰማዕት የሆኑ ምዕመናንን ማሰብ የሚገባን በመሆኑ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም የመታሰቢያ ዕለት ሆኖ እንዲውል ተወስኗል ነው ያሉት። በመታሰቢያ መርኃ ግብሩና በጸሎተ ፍትሀቱም የሰማዕታት ቤተሰቦች ተገኝተው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply