መቀሌ የታገቱ ‹‹ፌዴራሎች›› ጉዳይና ፌዴራሊዝም (ቢንያም መንበረወርቅ)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/45302

መቀሌ የታገቱ ‹‹ፌዴራሎች›› ጉዳይና ፌዴራሊዝም (ቢንያም መንበረወርቅ)
የፌዴራል መንግስቱ ሥልጣን በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ብቻ ታጥሮ የሚቀር፤ ከዛ ውጭ ባሉት የአገሪቱ ክፍሎች ያለው ተሳትፎ ግን በክልሎች በጎፍቃድ ላይ የሚመሰረት አድርጎ የሚያስብ ሰው ቁጥር በርከት ያለ ነው፡፡ ፌዴራል መንግሥት ማለት አዲስ አበባና ድሬዳዋ ብቻ የሚመስለውም ሰው እንዲሁ ትንሽ አይደለም፡፡ እውነታው ግን በፍጹም ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የፌዴራል መንግስት(የጋራው መንግሥት)ና የክልል መንግሥታት መካከል ያለው ክፍፍል ሥልጣንን እንጅ መልካምድርን መሠረት ያደረገ አይደለም፡፡ የፌዴራሉ መንግስት በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን የሚያወጣቸው ሕጎችና መመሪያዎች ተግባራዊነታቸው በመላው ኢትዮጵያና በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ ነው፡፡ የፌዴራሉ መንግስት የሚያስተዳድራቸው የተለዩ ፌዴራል ዜጎች የሉትም፡፡ የፌዴራሉ መንግስት ዜጎች ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በተሰጣቸው ስልጣን የሚያስተዳድሩዋቸው ተመሳሳይ ኢትዮጵያውያን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.