መንግሥት የልዩነትን ክብሪት ከፋብሪካው ሊያጠፋ ይገባል፡፡ – የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/155282

‹‹የሕዝብ ያልሆነ ሐሳብ የበላይነት እየወሰደ ነው፤ መንግሥት የልዩነትን ክብሪት ከፋብሪካው ሊያጠፋ ይገባል፡፡›› የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
(አብመድ) ከሰሞኑ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተለያዩ ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡ ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎችም የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የማኅበረሰቡ ሠላማዊ እንቅስቃሴም ተገትቷል፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ ለዘመናት ተከባብረውና ተዋልደው የኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ስብጥር ማንነት፣ የተለያዬ ሃይማኖት፣ የበዛ ቋንቋ እና ባሕል ቢኖርም የእርስ በርስ ግጭት መንስኤ የሆነበት ዘመን ጎልቶ አይስተዋልም ነበር›› ያሉት የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ‹‹የሕዝብ ያልሆነ ሐሳብ የበላይነት እየወሰደ መሆኑ ለግጭት እየዳረገ ነው›› ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከተፈጠረው ግጭት በመነሳት መሰል ግጭቶች እንዳይከሰቱ አቅደው እየሠሩ መሆኑን የተናገሩት መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጣቶችን የማስተማር ሥራ እና የሃይማኖት ተቋማትን ከግጭት ነፃ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
‹‹እምነትና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል›› ያሉት መልአከ ሠላም ኤፍሬም በሃይማኖቶች መካከል ልዩነትን በመፍጠር ወደ ግጭት እንድንገባ የሚጥሩ አካላት አንድነታችን ይበልጥ ያጠነክሩታል፤ መንግሥት ችግሩን በዝምታ ከመመልከት እና ችግር ሲፈጠር እሳት ለማጥፋት ከመሯሯጥ ይልቅ የልዩነትን ክብሪት ከፋብሪካው ሊያጠፋ ይገባል›› ብለዋል፡፡
ሕዝቡ በምሕላ ጸሎት እና በሠላማዊ ሰልፍ ያለምንም ልዩነት አንድ መሆኑን ባሳየበት መንፈስ ችግር ፈጣሪዎችን በመምከር፣ በመከላከል እና በመገሰፅ ኅብረቱን ሊያሳይ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ግባኤው በመግለጫው ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች በየቤተ እምነቶቻቸው ስለሠላም እንደሚያስተምሩ እና ወላጆቻቸውን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.