መንግስት ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ያደርግ የነበረውን የግብር ቅናሽ አቆመ

Source: http://wazemaradio.com/%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8C%88%E1%88%88%E1%8C%88%E1%88%89-%E1%89%B0%E1%88%BD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%AD/

ዋዜማ ራዲዮ- መንግስት ያገለጉሉ መኪናዎች ከውጭ ሲገቡ ያደርግ የነበረውን የቀረጥ ስሌት ቅናሽ ከትላንት ጀምሮ አቆመ።
መንግስት ከዚህ ቀደም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ላለማበረታታት እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል በተባለ የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ መመሪያም ያገለገሉ መኪናዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ ለመኪናዎቹ ቀረጥ ሲከፈል ፣ ከተሽከርካሪዎቹ ዋና ዋጋ ላይ የአገልግሎት ዋጋ ተብሎ እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ የይደረግ የነበረውን የቀረጥ ስሌት እንዲተው አድርጓል።

በዚህም መሰረት ከአሁን በሁዋላ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ የሚከፍሉት ቀረጥ የሚሰላው ከዋና ዋጋቸው ላይ መኪናው ላገለገለበት እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ ሳይሆን በዋና ዋጋቸው ይሆናል ማለት ነው።ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡበት የነበረውን ማበረታቻ በእጅጉ ይጎዳዋል።የሀገር ውስጥ የመኪና ዋጋም ላይ ከፍተኛ ጭማሬን ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።

መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አዘው መመሪያው እስኪወጣ ያልገባላቸው አስመጪዎች በምን እንደሚታዩ ገና ግልጽ አልሆነም።መንግስት ይህን የታክስ አሰራር በማስቀረት ለነዳጅ ግዥ የሚያወጣውን ምንዛሬ ለመቀነስ እንዳሰበም ይነገራል።

የአዘጋጁ ማስታወሻ- የመመሪያውን ዝርዝር ዘግየት ብለን እንመለከተዋለን!

The post መንግስት ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ያደርግ የነበረውን የግብር ቅናሽ አቆመ appeared first on Wazemaradio.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.