መንግስት 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ መፈፀሙ ተገለፀ

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-400-%E1%88%BA%E1%88%85-%E1%88%9C%E1%89%B5%E1%88%AA%E1%8A%AD-%E1%89%B6%E1%8A%95-%E1%88%B5%E1%8A%95%E1%8B%B4-%E1%8C%8D%E1%8B%A2-%E1%88%98%E1%8D%88%E1%8D%80/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ መጠናቀቁን የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።

የግዢ ሂደቱ የተጠናቀቀው ይህ 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚሰጥ ነው ተብሏል።

የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደገለጹት የግዢ ሂደቱ ከተጠናቀቀው 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን በተጨማሪ በአሁን ወቅት ወደ ሃገር ውስጥ እየገባ የሚገኝ 200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ መኖሩን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ከተባለው የስንዴ ግዢ በተጨማሪ ለአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለእርዳታ የሚውል 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን የስንዴ ግዢ በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አቶ ይገዙ ዳባ ተናግረዋል።

 

በታሪክ አዱኛ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.