“መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” የሚለውን አሜን ብያለሁ  #ግርማ_ካሳ

Source: http://www.mereja.com/amharic/544901

ከነሃሴ 26 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2009 ዓ.ም በየቀኑ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዙሪያ ቀናቶች ታስበው እንዲዉሉ የኢሕአዴግ መንግስት ደንግጓል። ይሄ መርሃ ግብር “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” በሚል መሪ ቃል  ነው የተጀመረው። ነሃሴ 26 2009 ዓ.ም የፍቅር ቀን ፣ …

Share this post

One thought on ““መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” የሚለውን አሜን ብያለሁ  #ግርማ_ካሳ

 1. …ከነሃሴ ፳፮ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ ፭ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም በየቀኑ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዙሪያ ቀናቶች ታስበው እንዲዉሉ የኢሕአዴግ መንግስት ደንግጓል። ይሄ መርሃ ግብር “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” በሚል መሪ ቃል ነው የተጀመረው።…ይሄን መርሃ ግብር ብዙ ወገኖች ብዙ ትኩረት የሰጡት አይመስልም። እንደውም ሲያጣጥሉት ነው እያየን ያለነው!?። ምክንያቱም ነቄ ትውልድ ነው። “ይህም ትውልድ ፍም እሳት ነው” አሉ ለመሆኑ ፍቅር በአስቸኳይ አዋጅ አለን?
  ፵፫ ዓመት ልዩነታችን ውበታችን የተሰበከ ትውልድ፡ ድንገት አንድነታችን ጥንካሬችን!መንገደኛውን ሠላም በል!የጭራቅ ባንዲራ ይዘህ ነጭ ልብስ! ሞዴሎች አበባ ይበተናሉ! የከተማው ከንቲባ ለባለሥልጣናት ካርድና አበባ በመላክ ይሞሳሞሳሉ! የሚሉ የየት ሀገር ኩረጃ? (ኮፒ ፔስት) ቆርጦ ቀጥልነት ውሸታምነት ነው?

  ** በእርግጥ ከጫካው ማኒፌስቶ፡ ከደደቢት በረሃ ከማሌሊት ርዮተ ዕምነት አልባነት፡ ትውልድን ማምከንና ማባከን፡ …ታሪክን መሰረዝና መደለዝ…ዘር ማጥፋትና ሀገር መሸጥ ፍቅር፡ሠላም፡ ዕወቀት፡ መከባበር፡ አብሮ መኖር፡አንድነት፡የሀገር ፍቅርና ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም እስኪል ትውልዱን የዕጽና ሴሰኝነት ተጠርናፊ ጀዝባ ማድረጋቸውን ማመናቸው በራሱ ትልቅነት ነው። በነገራችን ላይ ክቡር ፕሬዘዳንቱ ቱርክ ሆነው ተሾመው ያልሰሩትን ዓመታዊ እሪፖርት ድንገት እንዲያነቡ የተገደዱት ሳያንስ…በሥራ ዘመናቸው የንጹሓን ሕይወት ሲጠፋ፡ሀገር በተቃውሞ ሲታመስ፡ ምክርና መፍትሄ ሳያፈላልጉ የጠፋውን ንብረት አመዱን ጎብኝተው፡ በማግስቱ ኢንቨስተር ለማፈላለግ ጥሊያን መሄዳቸው ሳያንስ፡ ሟች እንጂ ገዳይ ባልታወቀበት የእሬቻ በዓል ላይ ድንጋይ በሲሚንቶ አቁመው፡ የሠላምና ፍቅር ቀን ማለታቸው እጅጉን ዘግናኝ አሳፋሪ ተግባርና ከንቱ ትምህርት ነው ድሮስ የቻይና ትምህርትና ዕቃ ባትሉኝ!።
  **ይቺው የተፈጠፈጠች ኢትዮጵያ “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው!”ያስፈነደቃቸው ሰዎች ትርጉሙ ገብቶአቸዋል?

  __ ነገሩ እንዲህ ነው”ያለፈው ፲ ዓመት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ በልማት፡ የአካባቢው ጸጥታ አስከባሪነት ተጠሪ መሆኗ ፡የአፍሪካ ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንባታ ቀዳሚ መሆኗ፡ ችግርና ድርቅን ሳትለምን በራሷ መከላከሏ ርሃብ ባለመኖሩ፡ በዩኒቨርሲቲ ግንባታና የተማሪ ቁጥር ብዛት፡ ከተለያዩ ግድብ ለጎረቤት መብራት መሆኗ፡ ከማናቸውም ዕድገት ከጎረቤት ሀገራት ተካፍላ በመብላቷ፡ ፲፩ ከመቶ ድርብ ኅሀዝ ዕድገት ጤፍ በልተው ስኳር ልሰው የማያቁ ተጠቃሚ መሆናቸው፡ ይኸው ዕድገት በእየ ክልሉ ጥሩ ጥሩ ሙሰኞች፡ አውርቶ አደሮች፡ ልዩ ጥቅማጥቅመኞች እንዲፈለፈሉ ማድረጉን በማሰብ በተገኘው ውጤት ሕዝቡ ደስታውን ለአሥር ቀን ያላቋረጠ ማጣጣም እንዲያደርግ መሬት የተሰጣቸው አበባ…ማተሚያ ቤት የተገነባላቸው ካርድና ቀን መቁጠሪያ፤ ግብር የማይከፈሉ ነጻ መጓጓዣና..አነስተኛ ተጠቃሚዎች አልባሳት…መካከለኛ ተጠቃሚዎች የበዓሉ ማድመቂያ የሚያዋጡ ሲሆን አድርባዮች ሚዲያውን እንዲቀውጡት ተደነገገ። አሁንም እኛው እንመራለን የጀመርነው እኛ ነን በእኛ ታልቃለህ ማለታቸው ነው ስለወደፊቱ አዲስ ነገር የለም!!!። ለመሆኑ ያ የፈረደበት ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች የት ናቸው? ምን ተጠቀሙ?ለመሆኑ ሀገሬ! ባሕሏ! ሃይማኖቶቿ! ታሪኳ!አብሮነት!መተዛዘን! ያሉ ለምን ታሰሩ? በአደባባይ ተሰድቡ? ተደበደቡ? ተሳደው ተሰደዱ? ተገደሉ?መጋባት መዋለድን ሃጢያት (የተዛባ ግንኙነት)ውግዝ ከማሃሪዎስ ሲል እንደከብት ጋጣ (ክልል)ከልሎ ከለከላቸው? ዛሬም ለዚሁ ዘረኝነት ጎጠኝነትና ጠባብነት ስገዱልኝ ማለታቸው ሕዝብ ይመርጠናል ምን አማራጭ አለው ማለታቸው…የሙስና ግልገሎችን ቀድመው ጭዳ ማለታቸው በራሱ ፈገግታን ያጭራል…የግርማ ሞገስ…አፍራሽ ገንቢ ሲሆን በሳቅ ፈራሽ ሲፈነዳ…ተገንቢ ደስ አለው ነቄ ካላለማ ምንድነው አራዳ!
  ኢትዮጵያዊነት ጸጋ ነው!ይህ የዋህና ጨዋ ሕዝብ ክብር እንጂ አብሮነትና የሀገር ፍቅሩን የዓለም ሕዝብ ይመሰክራል በለው!

  Reply

Post Comment