መፍትሄው! በህዝባዊ ማዕበል የቀውሱን ፈጣሪ ማስወገድ !! ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

Source: http://ethioforum.org/amharic/%E1%88%98%E1%8D%8D%E1%89%B5%E1%88%84%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A3%E1%8B%8A-%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%A0%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%8D%E1%88%B1%E1%8A%95-%E1%8D%88%E1%8C%A3/

ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND) ታሕሳስ 2017 ቀውሱ ከባድ ነው፣ ሃገርን ሊያፈራርስ፥ ህዝቦችን እርስበርስ ሊያዳም የሚችል ኣደገኛ ቀውስ ለመሆኑ በየቀኑ ከምንሰማቸው ዘግናኝና ኣሳዛኝ ድርጊቶች መገንዘብ ይቻላል። ይህ ኣስጨናቂ ክስተት በኣንድ ወቅት…

Share this post

One thought on “መፍትሄው! በህዝባዊ ማዕበል የቀውሱን ፈጣሪ ማስወገድ !! ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

 1. >›፡ከምንገኝበት ከባድ ቀውስ መውጫው አንድ በር ብቻ ነው ያለው። ይኸውም ተባብሮና ተቀናጅቶ፣ የጋራ ማዕከል ግንባር ፈጥሮ፥ ህዝባዊ ማዕበል ቀስቅሶ አምባገንኑን አገዛዝ ማስወግድና በቦታው መጀመርያ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያስተናግድ የጋራ መንግስታዊ ስርዓተ-ህዝብ (መንስህ) መመስረት ነው። ቀዋሚ መሰረት የሆነው፥ ይህ ስርዓት ተዋቅሮ ከቦታው ስለሌለ ነው፥ ማንም ቡድን እንደምንም ስልጣን ላይ እየወጣ እንዳሻው ረግጦ የሚገዛን። ማፍያዊው ቡድን ከተወገደ በኋላም ያንኑ ዓይነት ቡድን ተመልሶ እንዳይወጣብን አስቀድመን ስርዓቱን በጠንካራ መሰረት ላይ ማኖር ያስፈልገናል።
  ___ የሃገራችንን አንድነት በታኝ፥ ህዝቦቻችንን እርስበርስ ኣጨፋጫፊ ዋናው ስራኣስኪያጅ የህወሓት/ኢህአዴግ ማፍያዊ (ወሮ በላ) ቡድን ሆኖ እያለና ይህንን መዥገርት ለመንቀል የጭቁኑ ህዝብ ማዕበል ፈጥሮ መንቀሳቀስ ሲገባ፣ በቁንጽል አስተሳሰብ ተነሳስተው ያ መፍትሄ የሚሆነው ህዝባዊ ማዕበል እንዳይፈጠር የሚያሰናክሉ (አድርባይ!)ወገኖችን እርማትም ማስጠንቀቂያም እንዲደርሳቸው ያስፈልጋል። ተወደደም ተጠላ፥ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ፥ ማዕበሉ እንዳይፈጠር ሆድአደር!አውርቶ አደር! ልዩ ጥቅማጥቅመኛ! ሆነው ምክንያት እየሆኑ የአገዛዙን ዕድሜ ያስቀጥላሉና!!!

  በመጨረሻም ለትግራይ ህዝብና ልጆቹ ኣጭር መልእክት ማስተላለፍ እንፈልጋለን።

  ___ የትግራይ ህዝብ ሆይ! ቀደም ሲል ያካሄድከው ትግል ከጎስቋላው ኑሮ ተላቀህ በእኩልነት፥ በአንድነት፥ በሰላም ለመኖር ነበር። ሆኖም ትክሻህን ረግጦ ስልጣን ላይ የተቆናጠጠው ማፍያዊ(ወንበዴ) ቡድን፥ በስምህ እየነገደ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን የመከራ አረንቋ ውስጥ መክተቱ ብቻ ሳይሆን እርስበርሱም እንዲተላለቅ እያደረገ ነው። ክፋታቸው በዚህ አያቆምም፣ ይህን እነሱ ሆን ብለው የፈጠሩት ግጭት ምክንያት በማድረግ የመገንጠል መፍትሄ እንድታቀነቅን እያሴሩብህ ነው። ዓላማው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እየበዘበዙ ሲያላገጡበት ከነበረው ስልጣን ሲባረሩ፣ አንተውኑ ምሽግ በማድረግ የለመዱት ማላገጥ እንዲቀጥሉብት በመፈለግ ነው። ስለዚህ ይህን አደገኛ ሴራ ለማክሸፍና አፈና የሌለበት ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለመኖር፣ ብዙ ሰው ያልገባው ድርብርብ አፈና ቢጫንብህም ቅሉ፥ እንደምንም ተጋፍጠህ፥ ከታሪካዊው ወገንህ ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ተሰልፈህ ማዕበሉ ውስጥ ግባ። በውትድርና የተሰለፉት ልጆችህንም አስረዳቸው።የዘላቂው መፍትሄ አቅጣጫ ይህ ብቻ ነው።
  *እያንዳንዱና ሁሉም ክፍለሀገሩን ቢያፀዳ ሀገራችን ጥዱና ሠላም ትሆናለች! መልካም ምክር መልካም መንገድ ነው። ለግንጠላ እንቢኝ በል!!!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.