ማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ሴቶችን በተደራጀ መንገድ የማታለል ወንጀል እየተበራከተ መሆኑ ተጠቆመ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/191745

ማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ሴቶችን በተደራጀ መንገድ የማታለል ወንጀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠቆመ፡፡

Image may contain: 1 personበጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ጸጋ እንደገለጹት ከባለፈው አመት ነሀሴ ወር ጀምሮ በተደራጁ አጭበርባሪዎች በፌስቡክና በዋትስአፕ ብቻ 40 የሚደርሱ ሴቶች ተጭበርብረዋል ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ስለወንጀል አፈጻጸሙ ሲናገሩ የናይጀሪያና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በፌስቡክ አካውንት በከተማዋ የሚገኙ ሴቶችን ጎደኛ በማደርግና የስልክ ቁጥራቸውን በመለዋወጥ በዋትስ አፕ ደውለው ያወሯቸዋል፡፡
ታዲያ እንዚህ ሴቶች በቪዲዮ ሪከርድ ሲያወሩ እነሱ የሚያወሩት በአማርኛ ሲሆን የሚያወራቸው ሰው ነጭ በመሆኑ እንዴት አማርኛ እንደቻለ ሲጠይቁት ጎግል ትራንስሌተር አለኝ በማለት መልስ ይሰጣል፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆናቸውና ኢትዮጵያዊ ተባባሪ ስላላቸው አማርኛውን የድምጽ ቅጅ በመውሰድ ከነጩ ሰውየ ቪዲዮ የአፍ እንቅስቃሴያቸው ጋር አብሮ እንዲሄድ በኮምፒውተር የታገዘ ኤዲቲንግ በመስራት ቪዲዮውን ይልኩላቸዋል፡፡
ከዛም በደንብ ከተግባቡ በኋላ ላገባሽ እፈልጋለሁ ስለዚህ ስጦታ ልላክልሽ በማለት ሴቶቹን አሳምነው በዋትስ አፕ ወርቅ፣ አይፎን ስልኮችን ፣አፕል ኮምፒተሮችንና ሌሎች ጌጣጌጦችን ካስመረጧቸው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የላኩትን የእቃ ዝርዝር የሚያሳይ እውነት የሚመስል ነገር ግን ፎርጅድ ዶክሜንት ስካን አድረገው በመላክ ያሳምኗቸዋል፡፡
ከቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙት ሴት ተባባሪያዎቻቸው አማካኝነት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተደወለ በማስመሰልና ከውጭ ሀገር እቃ ተልኮልሻል ስለዚህ የላከልሽ አካል የመላኪያውን ብቻ በመሆኑ የከፈለው የመቀበያውን ብር መክፈል ይጠበቅብሻል ስለዚህ የአየር መንገዱ አሰራር ደግሞ ክፍያው የሚፈጸመው በባንክ አካውንት በመሆኑ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.