ማነው የተሾመው ሳይሆን ምን ለማድረግ ነው ሹመቱ ነው ትልቁ ጥያቄ #ግርማ_ካሳ

Source: http://www.mereja.com/amharic/565063

 

ለኦህዴድ ቅርበት ካላቸው ጦማሪዎች መካከል አንዱ ደረጄ ገረፉ ቱሉ ነው። የሚጽፋቸው ጽሁፎች ይመቹኛል። ከዚህም የተነሳ በመደበኛነት የምከታተለው ጦማሪ ነው። የአቶ ሃይለማሪያምን መልቀቅ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስተር ከኦህዴድ መሆን እንዳለበት ይከራከራል። “አንድ ነገር በጣም ግልፅ ነው። ቦታውን እንፈልገዋለን። ምክንያቱ ደግሞ አሁን ሀገሪቷንም ሆነ ኢህአዲግ የገጠመውን ችግር መፍታት የሚችል ብቃት ያለው፣በመላው ህዝብ ተቀባይነት ያለው እና በማንኛውም መልኩ legitimate የሆነ ሰው ማቅረብ የምንችለው እኛ ስለሆንን” ይላል ደሬጄ። ይመስለኛል እነ አቶ ለማ መገርሳን አስቦ ነው።

 

ሌላው የኦሮሞ አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ ደግሞ ከሚኔሶታ፣ ማን ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን እንዳለበት ሲጽፍ ” Appoint Lemma Megersa፣ Chairman of EPRDF and ( acting) PM immediately ” ይላል። ብዙ ጊዜ ከጃዋር ጋር አልስማም፤ ግን አሁን መስማማት ይኖርብኛል። ለአቶ ለማ መገርሳ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት የኔም ልብ ክፍት ነው። ምን አልባት ጃዋር ለማን የደገፈው ኦሮሞነትን መለኪያ በማድረግ ይሆናል። ወገንተኛ በመሆን። እኔ ግን አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆናቸው ላይ ችግር የሌለብኝ፣ ቄሮ ያምጻል ከሚል፣ ወይንም ኦሮሞ ስለሆኑና የዘር መለኪያ በማስቀመጥ አይደለም። ወገንተኛ ብሆን የሸገርን ልጅ ፈልጌ ነበር እርሱ ይሁን የምለው። ግርማ ሰይፉን !!!! ፡) ነገር ግን በትክክል ኦሮሞነትን ትተን በብቃት ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉትን ብንመዝን ከለማ የሚሻል ሰው ያለ አይመስለኝም። ካለ ለመስማት ዝግጁ ነኝ። (እርግጥ ነው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለ ሌላ ብቃት ያለው ሰው። በአሁኑ ወቅት ግን ከነ በረከት ስምኦን ጋር አንገት ለአንገት ተያይዞ እየተፋለመ ነው ያለው)።

 

ለማ መገርሳ እነ አባ ዱላ ገመዳ ያበሰበሱትን፣ ዘረኛ ድርጅትን በመቀየር ወደ አዲስ ምእራፍ ያሸጋገረ፣ ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀን የኢትዮጵያዊነት አዝማች የሆነ ሰው ነው። ያ ብቻ አይደለም ለህዝብ የሚጠነቀቅም ነው። አጋዚ ገብቶ ወጣቶችን እንዳይጨርስ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ብዙ ጊዜ እንዳይታወጅ አድርጓል። አሁን የታወጀዉንም ከነ አቶ ገዱ ጋር በመሆን እንደተቃወሙት ተዘግቧል።፣ አባ ገዳዎችን ይዞ ቄሮዎችን በማግባባት ነገሮችን ለማረጋጋት የሞከረ ሰው ነው። የቻለውን በቅንነትና በትህትና አድርጓል። ከዚህም የተነሳ በአሁኑ ወቅት በኢሕአዴግ ውስጥ ፣ በሕዝብና በተቃዋሚዎች ተቀባይነት ሊኖረው የሚችል ሰው ቢኖር አቶ ለማ ነው ብዬ አስባለሁ።

 

እርግጥ ነው ለማ መገርሳ የፓርላማ አባል አይደለም። በሕግ መንግስቱ አንቀጽ 73 መሰረት ጠቅላይ ሚኒስተር የሚመረጠው ከፓርላማ አባላት ነው። ስለዚህ አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስተር እንዳይሆን ሕጉ ይከለክለዋል ሊባል ይችላል። ለዚህም መፍትሄው ቀላል ነው። ጃዋር አንድ የጠቀሰው ነገር አለ። “acting” የሚል ቃል። በኔ እይታ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን የፓርላማ አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ልክ በትግራይ ክልል እንደተደረገው በፌዴራል ደረጃም ማድረግ ይቻላል። ዶር ደብረጽዮን የትግራይ ክልል ምክር ቤት አባል ስላልሆነ የክልሉ አስተዳዳሪ መሆን ስለማይችል፣ ምክትል አስተዳዳሪ ሆኖ ነው እየሰራ እንዳለው።

 

ሁለት ነገሮችን ላንሳና ላቁም።

 

አንደኛ – ክልሉ ሰፊ እንደመሆኑ ሁሉንም ችግሮች አቶ ለማ መፍታት አልቻለም። በተለይም በኦሮሚያ ያሉ የሌሎች ማህበረሰባትን መብቶች በማስከበር ዙሪያ፣ ደፍሮ በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የኦነግ ርዝራዦችን ተቋቁሞ ለዉጦችን ማምጣት ተስኖታል። አሁንም ሌሎች በኦሮሚያ ውስጥ ከኦሮሞው በታች ነው የሚቆጠሩት። ትልቅ የዘር መድልዎ አለ። አሁንም ሌሎች ማህበረሰባት በአማርኛ አገልግሎት ማግኘት፣ በክልሉ ሆን በዞንና ወረዳ ቀበሌዎች ተመርጠው ሆነ ተቀጥሮ መስራት አይችሉም። አሁንም ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ናት። አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሌሎች ማሀረሰባት ላይ በዘራቸው ምክንያት ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። ሌልች በኦሮሚያ ውስጥ ሁለተኛ ዜጎች ናቸው። አቶ ለማ ያንን ማስተካከል አልቻለም።

 

ሆኖም ግን ለማስተካከል ካለመፈለግ የተነሳ ሳይሆን በብዙ ነገሮች ከመወጠሩ የተነሳ እንደሆነ ቅርበት ካላቸው ሰዎች ተረድቻለሁ። እና ምን ማለት ፈልጌ ነው አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን ስል ከኢሕአደእግ ውስጥ ተሻለ ስለሆነ እንጂ ፣ በርሱ ላይ ቅሬታዎች ስለሌሉኝ አይደለም ማለቴ ነው። ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ቢደረግ፣ እነ አንዱዋለም አራጌ፣ እነ በላይ በፍቃዱ…እያሉ በምንም ተአምር ለማ መገርሳን ልመርጥ አልችልም።

 

ሁለተኛ – አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑ የአገር ችግር ይፈታል ማለት አይደለም። ሃይለማሪያም እንደሆነው አቶ ለማም በሕወሃት ደህንነቶች ከታጠረና ከተከበበ በቀላሉ ጥቅም የለሽ ሊሆን ይችላል። ትልቁ ነገር ማን ነው ጠቅላይ ሚኒስተሩን የሚይዘው ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስተሩን የያዘው ሰው ምንድን ነው የሚያደርገው የሚለው ነው። ሕወሃትን ያገለግላል ወይስ ህዝብን ያገለግላል ? የኔ ጥያቄ ማን ስልጣን ላይ ይቀመጥ የሚለው አይደለም ? “የኔ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡

 

1) ዘሬ ሳይጠየቅ ከሁሉም እኩል ሆኜ በሁሉም የአገሪቷ ግዛቶች ሳልሸማቀቅ፣ ሳልፈራ፣ በነጻነት የመኖር ዋስታን አለኝ ወይ ? በአሁኗ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ውጭ ደረቴን ነፍቼ መኖር አልችልም። ለምን ከአዲስ አበባ ዉጭ ያሉ ግዛቶች በሙሉ በዘር ተሸንሽነዋል። እኔ ደግሞ ዘሬ ኢትዮያዊነት ነው። ለምሳሌ ከላይም በትንሹ ለማንሳት እንደሞከርኩት በኦሮሚያ የስራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ ነው። ኦሮሚያም የኦሮሞዎች ብቻ ናት። አሁን ባለው የክልሉ ሕግ መንግስት መሰረት። በመሆኑም በአዳማ ሸገር ከተወለድኩት ከኔ ይልቅ ሃረርጌና አሩሲ ድንበር የተወለደው ጃዋር የበለጠ መብት አለው። ለምን እርሱ መጀመሮያ ኦሮሞ ስለሆነ እኔ ደግሞ መጀመሪያም መጨረሻም ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩኝ። አዳማ የተወለደ ጉራጌ አገርህ አይደለም እየተባለ፣ ጉርሱም የተወለደ ፣ አዋሽን ተሻግሮ የማያውቅ አዳማን የራሱ መሬቱ አድርጎ ይቆጥራል። ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ። ብድር ፣ መንግስታዊ ድጋፍ ካስፈለገ ከጉርሱም የመጣው እንጂ አዳማ የተወለደው ከክልሉ መንግስት አያገኝም። ለምን የሁሉም ነገር መለኪያው በኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞነት ስለሆነ።

 

2) ግፍ ሲፈጸምብኝ አቤት የምልበት ፍርድ ቤት አለ ወይ ?

 

3) እኔን የሚያሸብረኝ፣ በዉሸት ክስ የሚያስረኝ፣ ቶርቸር የሚያደርገኝ ሳይሆን እኔን የሚጠበቀኝ የፖሊስና የደህንነት ተቋማት አሉ ወይ ?

 

4) ፕሮፖጋንዳ የሚረጭ ሳይሆን በትክክል ለሕዝብ መርጃ የሚያቀርብ ሜዲያ አለ ወይ ?

Share this post

4 thoughts on “ማነው የተሾመው ሳይሆን ምን ለማድረግ ነው ሹመቱ ነው ትልቁ ጥያቄ #ግርማ_ካሳ

 1. Dear writer
  Your perception regarding Oromia is wrong. Oromia is z only region where all nations and nationalities are enjioyed freedom equal employement, use their language treated equaly with out discrimination. The oromo issues is not to be primership but to implement our abd federal system constitution properly, ensure propertional representstion in Federal institution, defence forces, security and intelegense. With regard to OLF its a dead organization that was beried in Asmera. Hence be it OLF , ODF and IFLO are history. Lema is proactive pragmatist politician who could salvage Ethiopian unity. He is the first regional leader who revitalized Ethiopian unity. Although he is not interested to become PM but please note that he is the only unifyer who could reachout all nations and nationalities.
  M Abdi

  Reply
  1. i disagree with your sentence ”
   Oromia is z only region where all nations and
   nationalities are enjioyed freedom equal
   employement, use their language treated equaly
   with out discrimination.” that’s totally false.

   Reply
 2. Girma, you always like to talk controversial things. Please understand the slogan of the day -remove woyanies. You are trying to pull the people’s struggle one step backwards.

  Reply
 3. ትክክል ኖት አቶ በረከት ዶክተር አቢይ አህመድ በእርግጥ እርሶ እንዳሉት ስልጣን ፍላጊ መሆኑን ድሮም ይታወቃል ፡፡ ነገር ግን
  የተከበሩ አቶ በረከት እርሶ ባስቀመጡት ጉዳይ ላይ አንዳንድ ማስተካከያ ለማድረግ ስለፈለኩ እና ከእርሶ ጋር የሚስማማበት ሀሳብ ለማስቀመጥ ፈልጌ ነው አስተያየት ለመስጠት የተነሳሁት የህዝበኝነት እንደገና ማቆጥቆጥ ስጋት በተለየ መልኩ በኦህዴድና በኢህዴን አመራሮች መንፀባረቁ ድርጅታችሁ ኢህአዴግ የገጠመው አዲስ ፈተና መገላጫዎች ብዙ ቢሆኑም የዶክተር አብይ የምረጡኝ ዘመቻ ከኒው ሪበራሊዝም አስተሳሰብ ለይቼ አላየውም፡፡
  ስለ አብይ አንዳንድ ነገር ለማለት OBM በአማርኛ እና በኦሮምኛ ያቀረበው ዘገባ በርካታ ስህተቶች ይዞ ነው የወጣው
  1ኛ.አብይ በአጋሮ አከባቢ መወለዱ ትክክል ነው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ግን ጅማ አልተማረም በግንቦት 20 ት/ቤት (አግአዚ) አ.አ ሜክስኮ በ1994 ዓ/ም ነው የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው፡፡
  2ኛ. በ1983 ትግል አልገባም ይልቁንም በ1984 የአሰፋ ብርጌድ መቱ በነበረበት ወቅት አጋሮ ላይ ለአማን ከድር ጦፈኛ በመሆን ነው ወደ ድርጅቱ የተቀለቀለው እናም ብርጌድ ፍንጫአ ሆዴ ስትሄድ በፔሮል ከታቀፉት መንገሶች መካከል አብይ አንዱ ነው፡፡(ኮ/ል ጉደታ ኦፍጋሃን መጠየቅ ይቻላል)
  3ኛ. ኮ/ል ጉደታ ኦፍገሃ በአማን ከድር ጥያቄ መሰረት የሬድዮ ኦፕሬተር ሆነ ስልጠና ብርጌድ ቤኒ እያለች ወይም ከዚያ በኃላ አለምሸት ደግፍ መርቶት ወደ ሩዋንዳ በዘመተው ውጋገን ሻለቃ አባል ሆኖ ሩዋንዳ ተመደበ
  4ኛ የመከላከያ ሠራዊት በ1987 ሲቓቓም የተሰጠው ማዕረግ !/አለቃ ነበር በዚህ ማዕረግ እያለ ነው ወደ ግንቦት 20 አይደር ት/ቤት የገባው (በ1989 ሀምሌ ወር)
  5ኛ በ1990 የ9ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በሻብያ ወረራ ምክንያት ትምህርቱን አቓረጦ የሬድዮ ሞኒተር ሲግናል ተመድቦ እስከ ሰኔ 3 ውግያ እዝ ቆይቶ ኮ/ል ገ/ዋህድ ኪሮስ (ራሻይዳ) ወደ ጠለፋ ኦፕሬተር ላከው፡፡ አብይ የተመደበበት ቲም ሀላፊዎች እና ሙያተኞች በገጠማቸው አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ አብይ ከተማ መቅረቱ እውን ነው፡፡ በዚህ ወቅት ማዕረጉ %/አለቃ ነበር (ሲግናል ሬጅሜንት ሬጅሜንት ኃላፊዎችን ማናገር ይቻላል)፡፡
  6ኛ. ሳንቲም ላይና ማዕከል መታሰብያነት አብይን ከባድሜ አውጥቶ ጦር ኃይሎች ጀርባ ወደሚገኘው ሲግናል ሬጅሜንት አመጣው ከዛ ኢንሳ ሲመሰረት ይዞት ሄዶ እስከ 97 ዓ/ም ድረስም ያለው ማዕረግ መ/አ ነበር ከዚያ ጥሮተኛ መመርያ መሠረት ሌ/ኮ እንደደረሰ አልገባኝም ችግሩ የተቓሙ ነው፡፡
  7ኛ. ሳንቲምና አብይ ከአንድ ወር እስከ ሶስት ወር ለሚሆን ግዜ ደቡብ አፍሪካ ሄደው ነበር በሶስት ወር የሚያዝ ማስትረስ ግን አላቅም
  8ኛ. OBM በዘገበው በ1993 ማይክሮ ሊንክ በኮምፒዩተር ሳይንስ ዲግሪውን ይዟል ያለው በኢትዮጵያ የትምህረት ሕግ መሰረት ተቀባይነት ስለሌለው የትምህርት ማስረጃው ፎርጅድ ነው፡፡ ሰውየው ትምህርቱን የጨረሰው በ10ኛ ክፍል ሲሆን ዘመኑ ደግሞ 94 ከዚህ ስንነሳ 95 እና 96 ፕሪፓራቶሪ (የመሰናዶ ትምህርት) እንኳን ቢወስድ በ2000 ዓ/ም ነው የመጀመርያ ዲግሪውን ሊይዝ የሚችለው ስለዚህ እስከ 2000 ዓ/ም ያለው ማንኛውም የማስትሬት ማስረጃ በኢትዮጵያ የትምህርት ህግ ተቀባይነት የለውም ስለዚህ አጣሪ ኮሚቴ ኢህአዴግ አቓቑሞ ሊያጣራልን ይገባል፡፡ ይህ ማለት የሰራ ዶክትሬትም ተቀባይነት የለውም ማለት ነው ለማጠቃለል ድርጅታችሁ ኢህአዴግ በአጭበርባሪዎች የተሞላ ስለሆነ ይፈተሽ፡፡
  አህመድ አወል

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.