ምን ያልተሰራ ጉድ አለ? ግን ምን ግድ አለን? ( ዮሃስ ሰ )

Source: https://mereja.com/amharic/v2/83824

አዲስ አድማስ
• አገር ተሳከረ። ኑሮ ከሰረ። የሰው ሕይወት ረከሰ።
• ዘረኝነት እየተዋዛ የአገሬው ምሳና እራት እስኪመስል ድረስ ቢሳካላቸው፣… ወይም ዘረኝነት በጥሬ እንደ ሰደድ እሳት አገሬውን
ከዳር ዳር እስኪያነድ ድረስ ምኞታቸው ቢሟላ፣… ከዚያስ አመድ ለመሆን ነው? ቢሳካልን ምን ይውጠናል?” ብለው አያስቡም ማለት ነው።
እዚህ አገር ያልተሞከረ የስህተትና የጥፋት አይነት የለም ሲሉ የተናገሩት ወደው አይደለም። ከአስቀያሚ እስከ አስፀያፊ፣ ከአሳፋሪ እስከ ወራዳ፣ እስከ ዘግናኝ ጭካኔ ድረስ… ብዙ ጥፋት ተሰርቷል – በድብቅና በግላጭ በአደባባይ፣ በተናጠልና በመንጋ።
ዝርፊያ፣ በአሳቻ ቦታና ሰዓት የሚፈፀም ወንጀል መሆኑ ቀርቶ፣ በዋና መንገድ በጠራራ ፀሐይ፣ በሞተርሳይክል አጀብና በሆታ፣ ቀልድና ጨዋታ እስኪመስል ድረስ አየን። መንገድ መዝጋት መብትን የሚጥስ ድርጊት መሆኑ ቀርቶ፣ በተገላቢጦሹ እንደ መብት ተቆጥሯል።
ህግንና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ የዜጎችን መብት ከመጠበቅ ይልቅ፣ ጥፋት የሚፈፅሙ ህግ አስከባሪዎች ላይ ማማረር ቀረና፣… ከተማ መንደሩ በወንጀለኞች ሲወረር – ነዋሪዎች ሲሰቃዩ፣ ሲደፈሩና ከህፃን እስከ አዛውንት እንደ እባብ ተቀጥቅጠው ሕይወታቸውን ሲያጡ፣… ህግ አስከባሪዎች አይተው እንዳላዩ፣ ምንም እንዳልተፈጠረና እንደማይመለከታቸው ሆነው ሲቀመጡ ተመለከትን።
ፖለቲካ፣… ኑሮን በነፃነት ለመምራት፣ ሕግና ሥርዓትን ለማስፈን ሊያገለግል እንደሚገባ ተረስቶ፣ የሰዎች ሕይወትና ኑሮ በመስዋዕትነት የሚገበሩለት የበላይ ጣዖት አስመስለነዋል። ኑሮና ሕይወት የፖለቲካ መቆመሪያ ሆነዋል።
በብሔር ብሔረሰብ ፖለቲካ ሳቢያ፣ አገሪቱ በአስፈሪ ፍጥነት የገደል አፋፍ ላይ መድረሷ፣ እጅጉን ሊያስጨንቃቸውና እንቅልፍ አጥተው መፍትሄ ለመፈለግና ለማበጀት በቅንነት፣ በእውነትና በትጋት እንዲጣጣሩ የሚጠበቅባቸው ምሁራንና ጋዜጠኞች፣ ከተቃዋሚውም፣ ከገዢውም ፓርቲ በርካታ ፖለቲከኞች፣… ይባስኑ፣ ዘረኝነትን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.