ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሳባውን አካሄደ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%89%A4%E1%89%B5/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአንደኛ መደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባቀረቡት ንግግር ላይ የድጋፍ ሞሽኑ አዳመጠ።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 28/2011 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ  ያቀረቡትን የመንግስትን አመታዊ እቅድ ነው ምክር ቤቱ ያደመጠው።

የድጋፍ ሞሽኑን  የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አማኑኤል አብርሃም ያቀረቡ ሲሆኑ፥ በ4ኛው የምክር ቤት የስራ ዘመን መንግስት በዋናነት ሊያከናውናቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን ማካተቱን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር  ዐብይ አህመድ የሚያቀርቡትን የመንግስት አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑ የሚጸድቅ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የምክር ቤቱ ሶስተኛ አመት የስራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ-ጉባኤ በመመርመር በሙሉ ድምጽ ምክር ቤቱ ማፅደቁ ታውቋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.