ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል

ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን በነገው ዕለት እንደሚያካሂድ ይጠበቃል
ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ተብሏል፡፡
በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡
በልዩ ስብሰባውም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 25፣2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽንን ያጸድቃል፡፡

The post ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply