ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን አወያዩ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/71445

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን አወያዩ

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ዑማና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት እንዲሁም የክፍለ ከተማ አመራሮች በከተማዋና እና በዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን አወያይተዋል፡፡
በውይይቱ መጀመርያ ኢንጅነር ታከለ ዑማ “የአርሶ አደሮችን ህይወት መቀየር ታሪካዊ ኃላፊነት የጣለብን ግዴታ ነው፤ ይህንን ታሪክ የጣለብንን ኃላፊነት እንወጣዋለን” ብለዋል፡፡
አርሶ አደሮችም አላግባብ ከቀያቸው ስለመፈናቀላቸው፣ ስለ ካሳ ክፍያና የማቋቋሚያ ድጎማ፣ ስለ መሰረተ ልማት አቅርቦት፣ ስለ ካርታ አሰጣጥና የአርሶ አደር ልጆች የካሳ ክፍያ፣ እንዲሁም በክፍለ ከተሞች ስላለው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ዑማ ጥያቄዎች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለም ከዚህ በኋላ በልማት ሰበብ የሚፈናቀልና የእርሻ መሬቱን የሚነጠቅ አርሶ አደር እንደማይኖር አረጋግጠውላቸዋል።
በእስካሁኑ ሂደት የተጎዱ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እና ህይወታቸውን ለመቀየር አስተዳደሩ ከምንም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራልም ብለዋል።
ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.