ሞሮኮ የአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር አስመረቀች

Source: https://fanabc.com/2018/11/%E1%88%9E%E1%88%AE%E1%8A%AE-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%8D%88%E1%8C%A3%E1%8A%91%E1%8A%95-%E1%89%A3%E1%89%A1%E1%88%A8-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%80%E1%89%BD/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን ሆነውን ባቡር የሀገሪቱ ንጉስ ሞሃመድ ስድስተኛ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተገኙበት አስመረቀች፡፡

ባቡሩ ኤልጂቪ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የኢንዱስትሪ ማዕከል ከሆነችው ካሳብላንካ ወደ ንግድ ከተማዋ ታንጊኤር 4 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ይፈጀ የነበረውን  ጉዞ በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ እንደሚጓዝ ተነግሯል፡፡

2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የፈጀው የባቡር ግንባታ ከሰባት ዓመታት በኃላ ነው የተጠናቀቀው፡፡

ሞሮካ ከፈረንሳይ ኩባንያ 12 ፈጣን ባቡሮችን እንደገዛችና  በአመት 6 ሚሊየን ሰዎችን ያመላልሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡

የባቡር ግንባታው የሀገሪቱን የትራንስፖር ዘርፍ ለማዘመንና  ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ እንደተከናወነ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.