ሞዚላ ቪፒኤን ያለው ፋየርፎክስ ብራውዘር እየሞከረ መሆኑ ተነግሯል

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%88%9E%E1%8B%9A%E1%88%8B-%E1%89%AA%E1%8D%92%E1%8A%A4%E1%8A%95-%E1%8B%AB%E1%88%88%E1%8B%8D-%E1%8D%8B%E1%8B%A8%E1%88%AD%E1%8D%8E%E1%8A%AD%E1%88%B5-%E1%89%A5%E1%88%AB%E1%8B%8D%E1%8B%98%E1%88%AD/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሉት ሞዚላ አሁን ደግሞ በፋየርፎክስ ብራውዘሩ ላይ አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል።

ይህም ቪፒኤን የተገጠመለት ሞዚላ ፋየርፎክስ የኢንተርኔት መክፈቻ  (ብራውዘር) ሲሆን፥ በአዲሱ ብራውዘሩ ላይም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አዲሱ የሞዚላ በራውዘር “Firefox Private Network” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ነው የተባለው።

አዲሱ የሞዚላ ፋየርፎክስ ቪፒኤን በራውዘር በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የሞዚላ ተጠቃሚዎች ዘንድ በሙከራ ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ታውቋል።

አዲሱ የሞዚላ ቪፒኤን ብራውዘር ተጨማሪ ቪፒኤን ድረ ገጾችን በኮምፒውተራችን ላይ መጫን ሳያስፈልግ በቀላሉ ለመጠቀም የሚያስችል ነው።

በዚህ የሞዚላ ቪፒኤን ብራውዘር አማካኝነትም ተጠቃሚዎች የግል መረጃዎቻቸውን ለጥቃት ሳይጋለጥ በድረ ገፆች ላይ ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.